Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 6:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር፣ ዋግ ወይም አረማሞ፣ አንበጣ ወይም ኵብኵባ በሚከሠትበት ጊዜ ወይም ከተሞቻቸውን ጠላት በሚከብብበት ጊዜ፣ እንዲሁም ማንኛውም ዐይነት ጥፋት ወይም በሽታ በሚደርስባቸው ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 “በምድር ላይ ራብ ወይም ቸነፈር ወይም ዋግ ወይም አረማሞ ወይም አንበጣ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ ጠላቶቻቸውም የአገሩን ከተሞች ከብበው ቢያስጨንቁአቸው፥ ማናቸውም መቅሠፍትና ደዌ ቢሆን፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፥ እንዲሁም የእህል ሰብል በሚያቃጥል ነፋስና በአንበጣ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ፥ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብህ ላይ ከበባ በሚያደርጉበት ጊዜ፥ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 “በም​ድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ፥ ወይም አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢሆን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ሩን ከተ​ሞች ከብ​በው ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸው፥ ማና​ቸ​ውም መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ቢሆን፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 “በምድር ላይ ራብ ወይም ቸነፈር ወይም ዋግ ወይም አረማሞ ወይም አንበጣ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ ጠላቶቻቸውም የአገሩን ከተሞች ከብበው ቢያስጨንቁአቸው፥ ማናቸውም መቅሠፍትና ደዌ ቢሆን፥

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 6:28
19 交叉引用  

በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ፣ ልጇ ከሞት ያስነሣላትን ሴት፣ “እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ የሰባት ዓመት ራብ ስለ ወሰነ፣ ተነሺና ለጊዜው መቈየት ወደምትችዪበት ቦታ ከቤተ ሰብሽ ጋራ ሂጂ” አላት።


ሕዝቅያስ እንዲህ ባለ ታማኝነት ነገሮችን ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ይሁዳን ወረረ። ድል አድርጎ የራሱ ሊያደርጋቸው በማሰብም የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ።


በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ ታምሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ እርሱም መለሰለት፤ ምልክትም ሰጠው።


ከሕዝብህ ማንኛውም ሰው ወይም መላው እስራኤል ጭንቀቱንና ሕመሙን ዐውቆ እጆቹን ወደዚህ ቤት በመዘርጋት ማንኛውንም ጸሎትና ልመና በሚያቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣


“ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣ በማዝዝበት ጊዜ፣ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር በምሰድድበት ጊዜ፣


እናንተ ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤ እናንተ የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤ የዕርሻው መከር ጠፍቷልና።


“በመካከላችሁ የሰደድሁት ታላቁ ሰራዊት፣ ትልልቁ አንበጣና ትንንሹ አንበጣ፣ ሌሎች አንበጦችና የአንበጣው መንጋ የበላውን፣ እነዚህ ሁሉ የበሏቸውን ዓመታት ዋጋ እመልስላችኋለሁ።


እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ በሽታ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኵሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።


ከእናንተ መካከል በመከራ ውስጥ ያለ አለ? እርሱ ይጸልይ፤ የተደሰተ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር።


መሳፍንት በሚገዙበት ዘመን፣ በምድሪቱ ላይ ራብ ሆነ፤ አንድ ሰው በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተ ልሔም ሚስቱንና ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ፣ ለተወሰነ ጊዜ ለመኖር ወደ ሞዓብ አገር ሄደ።


跟着我们:

广告


广告