2 ዜና መዋዕል 36:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንድሠራለት አዝዞኛል፤ ከሕዝቡ መካከል በእናንተ ዘንድ የሚገኝ ማንኛውም ሰው፣ እግዚአብሔር አምላኩ ከርሱ ጋራ ይሁን፤ እርሱም ወደዚያው ይውጣ።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ጌታ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም ይውጣ።’ ” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 የዐዋጁም ቃል እንዲህ የሚል ነው፤ “ይህ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት የቂሮስ ትእዛዝ ነው፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎኛል፤ በይሁዳ ውስጥ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ከተማ ለእርሱ ክብር ቤተ መቅደስን እሠራ ዘንድ ኀላፊነት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆናችሁ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሂዱ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሁን።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ እርሱም በይሁዳ ባለችው በኢየሩሳሌም ቤትን እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤ ከሕዝቡም ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ይውጣ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤ ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ይውጣ’” ብሎ በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ ደግሞም በጽሕፈት አደረገው። 参见章节 |