Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ኢዮስያስም እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆኑ በአጠቃላይ ሠላሳ ሺሕ በግና ፍየል እንዲሁም ሦስት ሺሕ ወይፈን ከንጉሡ ሀብት ሰጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም በሬዎች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሥ ኢዮስያስ በዚያው በፋሲካ በዓል የተገኙ ሰዎች መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቡአቸውን የራሱ ሀብት ከሆኑ የቀንድ ከብቶች፥ እንዲሁም የበግና የፍየል መንጋ፥ ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት ሺህ ወይፈኖችን ሰጠ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ኢዮ​ስ​ያ​ስም ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን በዚያ ለነ​በ​ሩት ለሕ​ዝቡ ልጆች ከመ​ን​ጋው ሠላሳ ሺህ የበ​ግና የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ሦስት ሺህም ወይ​ፈ​ኖች ሰጣ​ቸው፤ እነ​ዚ​ህም ከን​ጉሡ ሀብት ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም ወይፈኖች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:7
10 交叉引用  

ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።


ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤


የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ አንድ ሺሕ ወይፈን፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለጉባኤው ሰጠ፤ ሹማምቱም እንደዚሁ አንድ ሺሕ ወይፈን፣ ዐሥር ሺሕ በግና ፍየል ሰጡ። እጅግ ብዙ ካህናትም ራሳቸውን ቀደሱ።


በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ንጉሡ ጧትና ማታ እንደዚሁም በየሰንበቱ፣ በየወሩ መባቻውና በተወሰኑ በዓላት፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ከራሱ ንብረት ሰጠ።


ከዚያም የፋሲካውን በጎች ዕረዱ፤ ራሳችሁን ቀድሱ፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘውም መሠረት ዕርዶቹን ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”


ሹማምቱም ለሕዝቡ፣ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ በገዛ ፈቃዳቸው አዋጥተው ሰጡ። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቆች የሆኑት ኬልቅያስ፣ ዘካርያስና ይሒኤልም ለፋሲካ መሥዋዕት የሚቀርቡ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ በግ እንዲሁም ሦስት መቶ ወይፈን ሰጡ።


ጨዋ ግን ሐሳቡም ጨዋ ነው፤ በጨዋነት ምግባርም ጸንቶ ይገኛል።


በኢየሩሳሌም በዓላት ላይ እንደሚገኘው የመሥዋዕት በግ መንጋ አበዛዋለሁ። እነሆ! ፈራርሰው የነበሩት ከተሞች የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ይሆናሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”


በበዓላት፣ በወር መባቻና በሰንበታት፣ ለእስራኤል ቤት በተወሰኑት በዓላት ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ማቅረብ የገዢው ኀላፊነት ነው፤ ለእስራኤል ቤት ማስተስረያ እንዲሆንም የኀጢአት መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባል።’


跟着我们:

广告


广告