Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 32:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የሰናክሬም ሹማምትም በእግዚአብሔር አምላክና በባሪያው በሕዝቅያስ ላይ ከዚህ የከፋ ብዙ ነገር ተናገሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ባርያዎቹም ደግሞ አምላክ በሆነው በጌታና በባርያው በሕዝቅያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተናገሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የአሦር ባለሥልጣኖችም በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሕዝቅያስ ላይ ከዚህ የከፋ ነገር ተናገሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ደግሞ በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በባ​ሪ​ያው በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተና​ገሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ባሪያዎቹም ደግሞ በአምላክ በእግዚአብሔርና በባሪያው በሕዝቅያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተናገሩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 32:16
5 交叉引用  

አሁንም ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ አያስታችሁም። የየትኛውም አገር ሕዝብ ወይም መንግሥት አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ መታደግ የቻለ ስለሌለ አትመኑት። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!”


ንጉሡም እንደዚሁ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በመሳደብ፣ “የሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች አማልክት፣ ከእጄ እንዳልታደጉ ሁሉ፣ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊታደግ አይችልም” ሲል በርሱ ላይ ደብዳቤ ጻፈ።


አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤ አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል።


የላከኝን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ያደርጉባችኋል።


跟着我们:

广告


广告