2 ዜና መዋዕል 31:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም ስጦታውን፣ ዐሥራቱንና የተቀደሱ ስጦታዎቹን በታማኝነት አምጥተው አስገቡ። ሌዋዊው ኮናንያ የእነዚሁ ዕቃዎች ኀላፊ ሲሆን፣ ወንድሙ ሰሜኢ ደግሞ በማዕርግ ሁለተኛ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ቁርባኑና አሥራቱን የተቀደሱትንም ነገሮች በታማኝነት ወደዚያ አስገቡ። ሌዋዊውም ኮናንያ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ዐሥራቱንና በኲራቱን፥ የተቀደሱትንም ስጦታዎች ሁሉ በእምነት ወደዚያ አስገቡ፤ ኮናንያ ተብሎ የሚጠራው ሌዋዊ የዕቃ ግምጃ ቤቱ ኀላፊ ሆኖ ሲሾም፥ ወንድሙ ሺምዒ ደግሞ ረዳቱ ሆኖ ተሾመ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 መባኡንና ዐሥራቱን፥ የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡ። ሌዋዊውም ኮክንያስ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ቍርባኑንና አሥራቱን የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡት። ሌዋዊውም ኮናንያ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፤ 参见章节 |