Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 31:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ይህ ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ፣ በዚያ የነበሩት እስራኤላውያን ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው፣ የማምለኪያ ዐምዶችን ሰባበሩ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶች ቈረጡ፤ እንዲሁም በመላው ይሁዳና በብንያም፣ በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኰረብታ ላይ መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን አጠፉ፤ እስራኤላውያን እነዚህን ሁሉ ካጠፉ በኋላ ወደየከተሞቻቸውና ወደየርስታቸው ተመለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉንም ፈጽመው እስከሚያጠፏቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፥ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከበዓሉ ፍጻሜ በኋላ መላው የእስራኤል ሕዝብ ወደ ይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመሄድ ከድንጋይ የተሠሩትን የጣዖት ዐምዶች ሰባበሩ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የቆሙ ምስሎችንም ሰባብረው ጣሉ፤ መሠዊያዎችንና የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎችንም ደመሰሱ፤ እንዲሁም በቀሩት በይሁዳ፥ በብንያም፥ በኤፍሬምና በምናሴ ግዛቶች ውስጥ የነበሩትን የጣዖት መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ሁሉ አፈራረሱ፤ ከዚያም በኋላ ወደየመኖሪያ ስፍራዎቻቸው ተመለሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ይህም ሁሉ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ገኙ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወጥ​ተው ዐም​ዶ​ቹን ሰበሩ፤ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ች​ንም አፈ​ረሱ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አጠፉ። በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ሁሉ ደግ​ሞም በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ የነ​በ​ሩ​ትን ፈጽ​መው እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ አጠ​ፉ​አ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስ​ታ​ቸ​ውና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ተመ​ለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉን ፈጽመው እስካጠፉአቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፤ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 31:1
18 交叉引用  

ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋራ ዐብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት።


እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ ክፉ ሥራው ግን ከርሱ አስቀድሞ የነበሩት የእስራኤል ነገሥታት የፈጸሙትን ያህል አልነበረም።


ደግሞም፣ “በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን” የምትለኝ ከሆነ፣ የኰረብታ ላይ ማምለኪያዎቹንና መሠዊያዎቹን ሕዝቅያስ አፍርሶበት ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም፣ “እናንተ መስገድ ያለባችሁ በዚህ መሠዊያ ፊት ብቻ ነው” ብሎ የለምን?


በየኰረብታው ላይ ያሉትን የማምለኪያ ዐምዶች አስወገደ፤ አዕማደ ጣዖታትን ሰባበረ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶች ቈራረጠ፤ ሙሴ የሠራውን የናስ እባብ፣ እስራኤላውያን እስከ እነዚያ ጊዜያት ድረስ ዕጣን ያጤሱለት ስለ ነበር ሰባበረው፤ ይህም ነሑሽታን ይባል ነበር።


አሳ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር አደረገ፤


ባዕዳን መሠዊያዎችንና ማምለኪያ ኰረብቶችን አስወገደ፤ ማምለኪያ ዐምዶችን አፈረሰ፤ አሼራ ለተባለች ጣዖት አምላክ የቆሙ የዕንጨት ቅርጽ ምስሎችንም ቈራረጠ፤


ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት።


ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም፣ ‘በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፤ በላዩም መሥዋዕት አቃጥሉ’ በማለት የራሱን አምላክ የኰረብታ ላይ መስገጃ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችንስ ያስወገደ ሕዝቅያስ አይደለምን?


አባቱ ሕዝቅያስ ያፈራረሳቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያ ስፍራዎች መልሶ ሠራ፤ ለበኣሊም መሠዊያዎችን አቆመ፤ የአሼራንም ምስል ዐምዶች ሠራ፤ ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።


“ሂድና በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ በአንድነት ሰብስብ፤ ስለ እኔም ጹሙልኝ፤ ቀንም ይሁን ሌሊት ለሦስት ቀን አትብሉ፤ አትጠጡም። እኔና ደንገጡሮቼም እናንተ እንደምታደርጉት ሁሉ እንጾማለን፤ ይህ ከተፈጸመ በኋላ ግን ነገሩ ምንም እንኳ ከሕግ ውጭ ቢሆንም፣ ወደ ንጉሡ ዘንድ እሄዳለሁ፤ ከጠፋሁም ልጥፋ።”


ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም አታምልካቸው፤ ወይም ልምዳቸውን አትከተል፤ እነርሱን ማፈራረስ አለብህ፤ የአምልኮ ድንጋዮቻቸውንም ሰባብር።


መሠዊያዎቻቸውን ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቁ፤ የአሼራ ዐጸዶቻቸውንም ቍረጡ።


በእጃቸውም ወደ ሠሯቸው መሠዊያዎች አይመለከቱም፤ በጣቶቻቸው ላበጇቸው የዕጣን መሠዊያዎች፣ ለአሼራም የአምልኮ ዐምዶች ክብር አይሰጡም።


እንግዲህ በእነርሱ ላይ የምታደርጉት ይህ ነው፤ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የአሼራ ምስል ዐምዶቻቸውን ቍረጡ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።


跟着我们:

广告


广告