Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 3:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ፣ “ያኪን”፣ በስተሰሜን ያለውንም፣ “ቦዔዝ” ብሎ ጠራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፥ በቀኝም የነበረውን ስም ያኪን በግራም የነበረውን ስም ቦዔዝ ብሎ ጠራቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ምሰሶዎቹም የቆሙት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ግራና ቀኝ ነበር፤ በደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፥ በሰሜን በኩል የቆመው ደግሞ “ቦዔዝ” ተብሎ ይጠራ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አዕ​ማ​ዶ​ቹ​ንም አን​ደ​ኛ​ውን በቀኝ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ በቀ​ኝም የነ​በ​ረ​ውን ስም ርትዕ በግ​ራም የነ​በ​ረ​ውን ስም ጽንዕ ብሎ ጠራ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፤ በቀኝም የነበረውን ስም “ያቁም” በግራም የነበረውን ስም “በለዝ” ብሎ ጠራቸው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 3:17
4 交叉引用  

የስምዖን ልጆች፦ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው።


ዐምዶቹንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ላይ አቆመ፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ “ያኪን”፣ በስተሰሜን በኩል ያለውንም “ቦዔዝ” ብሎ ጠራው።


እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ሰንሰለቶች ሠርቶ ከዐምዶቹ ጫፍ ጋራ አገናኛቸው፤ ከዚያም መቶ የሮማን ፍሬዎች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋራ አያያዛቸው።


የመተላለፊያው በረንዳ ርዝመት ሃያ ክንድ፣ ከፊት እስከ ኋላ ያለውም ወርድ ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበር። ወደ ቤተ መቅደሱም የሚያደርሱ ዐሥር ደረጃዎች የነበሩ ሲሆን፣ በየዐምዱም ጐንና ጐን ምሰሶዎች ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告