Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 3:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ዳዊት ባዘጋጀው ቦታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሰሎሞንም ጌታ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የጌታን ቤት መሥራት ጀመረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሰሎሞን አባት ንጉሥ ዳዊት ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ስፍራ በኢየሩሳሌም በሞሪያ ተራራ ለይ አስቀድሞ አዘጋጅቶ ነበር፤ ይህም ስፍራ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት የተገለጠበት፥ ኢያቡሳዊው ኦርና አውድማ አድርጎ ይጠቀምበት የነበረ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በተ​ገ​ለ​ጠ​በት በአ​ሞ​ሪያ ተራራ ዳዊት ባዘ​ጋ​ጀው ስፍራ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 3:1
10 交叉引用  

ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።


እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይሥሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።


የእግዚአብሔር መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ የደረሰው ጕዳት እግዚአብሔርን ስላሳዘነው፣ ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ “በቃ! እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።


ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።


ከዚያም ዳዊት፣ “ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤ እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል” አለ።


ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤


በነገሠም በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ።


ነገር ግን የማደሪያውን ቤት የሠራለት ሰሎሞን ነበር።


跟着我们:

广告


广告