Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ የሚቀርበውን የኅብረት መሥዋዕት ሥብና የመጠጡን ቍርባን ጨምሮ የሚቃጠለው መሥዋዕት እጅግ ብዙ ነበር። በዚህ ሁኔታም የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንደ ገና ተደራጀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እጅግ ብዙ ከነበረው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የአንድነቱ መሥዋዕት ስብ ነበረ፤ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በዚያ ነበረ። እንዲህ ባለ መንገድ የጌታ ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ብዙ ከሆነው የሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርበው ስብ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የሚቀርበው የመጠጥ ቊርባን ነበር። በዚህ ሁኔታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት እንደገና ተጀመረ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ስብና ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ቀ​ር​በው የመ​ጠጥ ቍር​ባን ጋር ብዙ ነበረ። እን​ዲ​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ተዘ​ጋጀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የሚቃጠለውም መሥዋዕት የደኅንነቱም መሥዋዕት ስብ፥ ከሚቃጠለውም መሥዋዕት ሁሉ ጋር የሚቀርበው የመጠጥ ቍርባን፥ ብዙ ነበረ። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:35
11 交叉引用  

ያዕቆብም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት።


ጉባኤውም ያመጣው የሚቃጠለው መሥዋዕት ብዛት ሰባ ወይፈኖች፣ መቶ አውራ በጎችና ሁለት መቶ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ናቸው፤ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ ነበሩ።


ሕዝቅያስና ሕዝቡ፣ ነገሩ ሁሉ እንዲህ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲከናወን እግዚአብሔር ስለ ረዳቸው ሐሤት አደረጉ።


በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላክ አገልግሎት ካህናቱን በየማዕረጋቸው፣ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቧቸው።


ከዚያም በሆድ ዕቃዎች ያለውን ስብ ሁሉ፣ የጕበቱን መሸፈኛና ሁለቱንም ኵላሊቶች በዙሪያቸው ካለው ስብ ጋራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥላቸው።


ከዚህም ጋራ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን ሁለት ዐሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ለእህል ቍርባን፣ አንድ አራተኛ የሂን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን አቅርቡ።


“ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”


ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዐት ይሁን።


跟着我们:

广告


广告