Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆኑትን ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቡ፤ እነርሱም እጆቻቸውን ጫኑባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆኑትን አውራ ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቡ፥ እጃቸውንም ጫኑባቸው፥ ካህናቱም አረዱአቸው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ከዚህ በኋላም ፍየሎቹን ወደ ንጉሡና ወደተሰበሰቡት ሰዎች አቀረቡአቸው፤ ንጉሡና ሰዎቹም እጃቸውን ጫኑባቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ኑ​ት​ንም አውራ ፍየ​ሎች በን​ጉ​ሡና በጉ​ባ​ኤው ፊት አቀ​ረቡ፤ እጃ​ቸ​ው​ንም ጫኑ​ባ​ቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የኃጢያትም መሥዋዕት የሚሆኑትን አውራ ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቡ፤ እጃቸውንም ጫኑባቸው፤ ካህናቱም አረዱአቸው፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:23
6 交叉引用  

የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ በሚቀርበው እንስሳ ራስ ላይም እጁን ይጫን፤ ይህም ያስተሰርይለት ዘንድ በምትኩ ተቀባይነት ያገኛል።


የሕዝቡም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ፊት እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫኑ፤ ወይፈኑም በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ።


እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበትም ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ይህም የኀጢአት መሥዋዕት ነው።


እጁን ለኀጢአት መሥዋዕት በቀረበችው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራም ይረዳት።


እጁን በጠቦቷ ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራም የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረዳት።


ወይፈኑን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫን፤ በእግዚአብሔርም ፊት ይረደው።


跟着我们:

广告


广告