Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 26:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አሞናውያን ለዖዝያን ግብር ገበሩለት፤ ኀይሉ ስለ ገነነም ዝናው እስከ ግብጽ ዳርቻ ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብጽ መግቢያ ድረስ ተሰማ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዐሞናውያንም ለዖዝያ ገበሩለት፤ እጅግ እየገነነ በመሄዱ ዝናው እስከ ግብጽ ድረስ ተሰማ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሞ​ና​ው​ያ​ንም ለዖ​ዝ​ያን ገበሩ፤ እጅ​ግም በር​ትቶ ነበ​ርና ዝናው እስከ ግብፅ መግ​ቢያ ድረስ ተሰማ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አሞናውያንም ለዖዝያን ገበሩ፤ እጅግም በርትቶ ነበርና ዝናው እስከ ግብፅ መግቢያ ድረስ ተሰማ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 26:8
14 交叉引用  

“ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ።


ትንሿ ልጁም እንደዚሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ ብላ ጠራችው፤ እርሱም የዛሬዎቹ አሞናውያን አባት ነው።


ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።


እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።


እርሱም ከማንም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፣ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታን፣ ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደግሞም ከደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አሕዛብ ሁሉ ተሰማ።


ከዚህም የተነሣ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።


ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።


ከዚህ በኋላ ሞዓባውያንና አሞናውያን ከጥቂት ምዑናውያን ጋራ ሆነው ኢዮሣፍጥን ለመውጋት መጡ።


ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማእዘኑ በር፣ በሸለቆው በርና በቅጥሩ ማእዘን ማማዎች ሠርቶ መሸጋቸው።


ኢዮአታም የአሞናውያንን ንጉሥ ወግቶ ድል አደረጋቸው። በዚያ ዓመትም አሞናውያን አንድ መቶ መክሊት ጥሬ ብር፣ ዐሥር ሺሕ ቆሮስ ስንዴና ዐሥር ሺሕ ቆሮስ ገብስ ገበሩለት። አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።


ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


ከየትኛውም የአሞናውያን ምድር ለእናንተ ርስት ስለማልሰጣችሁ፣ አሞናውያን ዘንድ በደረሳችሁ ጊዜ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው። ያን ቦታ ርስት አድርጌ ለሎጥ ዘሮች ሰጥቻቸዋለሁ።”


አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፣ “ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን አድርግ፣ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።


跟着我们:

广告


广告