Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 26:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በእነዚህም የሚመራ ሦስት መቶ ሰባት ሺሕ ዐምስት መቶ ሰው ያለው ሰራዊት አለ፤ ይህም ንጉሡ በጠላቶቹ ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ለመሰለፍ የሚበቃ ጠንካራ ኀይል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ንጉሡንም በጠላቱ ላይ እንዲያግዝ፥ በታላቅ ኃይል ወደ ጦርነት የሚወጣ፥ በትእዛዛቸው ሥር የነበረ ሠራዊት ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በእነርሱም ሥልጣን ሥር የንጉሡን ጠላቶች ለመመከት በቂ ችሎታ ያላቸው ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ሠራ​ዊት ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ንጉ​ሡን በጠ​ላቱ ላይ የሚ​ያ​ግዙ፥ በታ​ላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ንጉሡንም በጠላቱ ላይ ያግዝ ዘንድ፥ በታላቅ ኃይል ወደ ሰልፍ የሚወጣ፥ ከእጃቸው በታች የነበረ ሠራዊት ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 26:13
9 交叉引用  

ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የእስራኤልን ቤት ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም እንዲመልሱ ከይሁዳና ከብንያም ቤት አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ወታደሮች ሰበሰበ።


ሮብዓም መንግሥቱን ከመሠረተና ካጸና በኋላ፣ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ።


አብያ አራት መቶ ሺሕ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ ዘመተ፤ ኢዮርብዓምም ስምንት መቶ ሺሕ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ በመውጣት ጠበቀው።


እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ አላቸው፤ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ማማ፣ መዝጊያና መወርወሪያ ያላቸውን ቅጥሮች በዙሪያቸው እናብጅ። አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም የኛው ናት፤ እኛ ፈለግነው፤ እርሱም በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጠን” እነርሱም ሠሩ፤ ተከናወነላቸውም።


አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የያዙ ሦስት መቶ ሺሕ የይሁዳ ሰዎች እንዲሁም ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺሕ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።


አሜስያስ የይሁዳን ሕዝብ በአንድነት ሰብስቦ፣ እንደየቤተ ሰቡ በሻለቆችና በመቶ አለቆች በመደልደል በመላው ይሁዳና በብንያም መደባቸው። ከዚያም ዕድሜያቸው ሃያና ከሃያ በላይ የሆናቸውን ሰብስቦ፣ ለውትድርና አገልግሎት ብቁ ሆነው ጋሻና ጦር መያዝ የሚችሉ ሦስት መቶ ሺሕ ሰዎች አገኘ።


በተዋጊዎቹ ላይ የተሾሙት የየቤተ ሰቡ መሪዎች ጠቅላላ ቍጥር ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበር።


ዖዝያን ለሰራዊቱ ሁሉ ጋሻ፣ ጦር፣ የራስ ቍር፣ ጥሩር፣ የቀስት ማስፈንጠሪያ ደጋንና የሚወነጨፍ ድንጋይ አደለ።


跟着我们:

广告


广告