2 ዜና መዋዕል 25:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እርሱ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤልም ሆነ ከማናቸውም የኤፍሬም ሕዝብ ጋራ አይደለምና፣ እነዚህ የእስራኤል ወታደሮች ከአንተ ጋራ አይዝመቱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 አንድ የእግዚአብሔር ሰው ግን ወደ እርሱ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ንጉሥ ሆይ! ጌታ ከእስራኤልና ከኤፍሬም ልጆች ጋር አይደለምና የእስራኤል ሠራዊት ከአንተ ጋር አይውጣ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ነገር ግን አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አሜስያስ መጥቶ “እግዚአብሔር ከኤፍሬምም ሆነ ከማንኛውም የእስራኤል ሕዝብ ጋር ስላልሆነ እነዚህን የእስራኤል ወታደሮች ይዘህ አትዝመት” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 አንድ የእግዚአብሔር ሰው ግን ወደ እርሱ መጥቶ፥ “ንጉሥ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤልና ከኤፍሬም ልጆች ሁሉ ጋር አይደለምና የእስራኤል ጭፍራ ከአንተ ጋር አይውጣ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 አንድ የእግዚአብሔር ሰው ግን ወደ እርሱ መጥቶ “ንጉሥ ሆይ! እግዚአብሔር ከእስራኤልና ከኤፍሬም ልጆች ጋር አይደለምና የእስራኤል ጭፍራ ከአንተ ጋር አይውጣ። 参见章节 |