Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 25:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የእስራኤል ንጉሥ ዮአስም የአካዝያስን የልጅ ልጅ የኢዮአስን ልጅ የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስን ቤትሳሚስ ላይ ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ ከኤፍሬም በር እስከ ማእዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ ያህል ርዝመት ያለውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን በቤት-ሳሚስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር ከኤፍሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈረሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ንጉሥ ዮአስም አሜስያስን ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ ከኤፍሬም ቅጽር በር አንሥቶ እስከ ማእዘን ቅጽር በር ድረስ ያለውን ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር ያኽል የሆነውን የኢየሩሳሌምን ቅጽር አፈረሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን በቤትሳሚስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር ከኤፍሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈረሰ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 25:23
18 交叉引用  

የእስራኤል ንጉሥ ዮአስም የአካዝያስን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአስን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ቤትሳሚስ ላይ ማረከው። ከዚያም ዮአስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ ከኤፍሬም ቅጥር በር አንሥቶ የማእዘን ቅጥር በር እስከ ተባለው ድረስ ርዝመቱ አራት መቶ ክንድ ያህል ርዝመት ያለውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ።


እነርሱም በይሁዳ ላይ ወጡ፤ ወረሯትም። በንጉሡ ቤተ መንግሥት የሚገኘውን ዕቃ ሁሉ፣ ከወንዶች ልጆቹና ከሚስቶቹ ጋራ ወሰዱ፤ ከመጨረሻ ልጁ ከአካዝያስ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም።


ከዐረቦች ጋራ ወደ ሰፈር የመጡት ወራሪዎች፣ ታላላቅ ወንድሞቹን ሁሉ ገድለዋቸው ስለ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይሆራምን የመጨረሻ ልጅ አካዝያስን በአባቱ ምትክ አነገሡት። ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ መግዛት ጀመረ።


ስለዚህ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በመቍሰሉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።


ይሁዳ በእስራኤል ድል ሆነ፤ እያንዳንዱም ወደ ድንኳኑ ሸሸ።


ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማእዘኑ በር፣ በሸለቆው በርና በቅጥሩ ማእዘን ማማዎች ሠርቶ መሸጋቸው።


ከዚህ በኋላም ንጉሡ ጠንክሮ በመሥራት፣ ከቅጥሩ የፈራረሱትን ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ማማ ሠራበት፤ በውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር በመገንባት የዳዊትን ከተማ ድጋፍ እርከን አጠናከረ፤ እንደዚሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን ሠራ።


ስለዚህ እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ እነርሱም በምናሴ አፍንጫ መንጠቆ አገቡበት፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


በጸደይም ወራት ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ካላቸው ዕቃዎች ጋራ ወደ ባቢሎን ወሰደው። የዮአኪንን አጎት ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በርሱ ላይ ዘመተ፤ ወደ ባቢሎንም ይወስደው ዘንድ በናስ ሰንሰለት አሰረው።


ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ በጎች በር ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም በዘበኞች በር አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ።


ስለዚህ ሕዝቡ ወጥተው ቅርንጫፎች አመጡ፤ እያንዳንዳቸውም በየቤታቸው ጣራ ሰገነት፣ በየግቢያቸው፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ፣ “በውሃ በር” አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳስ ሠሩ።


ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።


ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን ይጐናጸፋል።


“እነሆ ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማእዘኑ በር ድረስ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ይህች ከተማ ለእግዚአብሔር የምትሠራበት ጊዜ ይመጣል፤


የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለ ሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።


አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።


ምክንያቱም ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱንም ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ከፍ ይላል።”


跟着我们:

广告


广告