Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 25:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የይሁዳ ሰራዊት ሌሎች ዐሥር ሺሕ ሰዎች ማረኩ፤ ወደ አንድ ዐለት ዐናት ላይም አውጥተው ቍልቍል ለቀቋቸው፤ ሁሉም ተፈጠፈጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የይሁዳም ልጆች ደግሞ ዐሥር ሺህ ሰዎችን በሕይወታቸው ማረኩ፥ ወደ ዓለቱም ራስ ላይ አመጡአቸው፤ እነርሱንም ከዓለቱ ራስ ላይ ጣሉአቸው፥ ሁሉም ተፈጠፈጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሌሎች ዐሥር ሺህ ወታደሮችንም ማረኩ፤ እስረኞቹንም ሴላዕ ተብላ በምትጠራው ከተማ አጠገብ በሚገኘው ገደል አፋፍ ላይ አውጥተው ጣሉአቸው፤ ሁሉም ከገደሉ በታች በሚገኙ አለቶች ላይ ተፈጥፍጠው ሞቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የይ​ሁ​ዳም ልጆች ደግሞ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ማረኩ። ወደ ዐለ​ቱም ራስ ላይ አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ከዐ​ለ​ቱም ራስ ላይ ጣሉ​አ​ቸው፤ ሁሉም ተፈ​ጠ​ፈጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የይሁዳም ልጆች ደግሞ አሥር ሺህ ሰዎችን በሕይወታቸው ማረኩ፤ ወደ ዓለቱም ራስ ላይ አመጡአቸው፤ ከዓለቱም ራስ ላይ ጣሉአቸው፤ ሁሉም ተፈጠፈጡ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 25:12
8 交叉引用  

እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ የብረት መቈፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፣ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በሌሎቹ የአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሰራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


በዚያ የነበረውንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው። ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረገ። ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


“እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ግዛታቸውን እንዳይወርሩባቸው በማድረግህ ከእነርሱ ተመልሰው ሳያጠፏቸው የቀሩት የአሞን፣ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሰዎች እነሆ እዚህ አሉ።


አሜስያስም ኀይሉን በሚገባ አደራጅቶ ሰራዊቱን ወደ ጨው ሸለቆ መራ፤ በዚያም ዐሥር ሺሕ የሴይር ወታደሮችን ገደለ።


በዚያ ጊዜ አሜስያስ ያሰናበታቸውና በጦርነቱ እንዳይካፈሉ የከለከላቸው ወታደሮች፤ ከሰማርያ እስከ ቤትሖሮን ያሉትን የይሁዳ ከተሞች ወረሩ፤ ሦስት ሺሕ ሰው ገደሉ፤ እጅግ ብዙ ምርኮም ወሰዱ።


የእግዚአብሔርም ቍጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፤ ነቢይንም ላከበት፤ ነቢዩም፣ “የገዛ ሕዝባቸውን ከእጅህ ማዳን ያልቻሉትን የአሕዛብን አማልክት ርዳታ የጠየቅኸው ለምንድን ነው?” አለው።


ሹማምንታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፤ ቃሌ የምታረካ ናትና ይሰሟታል።


跟着我们:

广告


广告