2 ዜና መዋዕል 22:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በመቍሰሉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ከሶርያም ንጉሥ ከአዛኤል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቁስል ለመታከም ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ስለዚህ ከቊስሉ ለመፈወስ ተመልሶ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ፤ አካዝያስም ኢዮራምን ለመጠየቅ ወደዚያ ሄደ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ከሶርያም ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ከሶርያም ንጉሥ ከአዛኤል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። 参见章节 |