Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 22:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዐረቦች ጋራ ወደ ሰፈር የመጡት ወራሪዎች፣ ታላላቅ ወንድሞቹን ሁሉ ገድለዋቸው ስለ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይሆራምን የመጨረሻ ልጅ አካዝያስን በአባቱ ምትክ አነገሡት። ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ መግዛት ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በኢየሩሳሌም የነበሩትም ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ገድለዋቸው ነበርና። የይሁዳም ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዐረቦችና ተከታዮቻቸው ወረራ ባደረጉ ጊዜ በሰፈሩ ላይ አደጋ ጥለው ከሁሉ ታናሽ ከሆነው ከአካዝያስ በቀር የንጉሥ ኢዮራምን ወንዶች ልጆች በሙሉ ገደሉ፤ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ አካዝያስ በአባቱ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ አደረገ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የነ​በ​ሩት ታና​ሹን ልጁን አካ​ዝ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። የመ​ጣ​ባ​ቸው የዓ​ረ​ብና የአ​ሊ​ማ​ዞን የሽ​ፍ​ቶች ጭፍራ የእ​ር​ሱን ታላ​ቆች ወን​ድ​ሞች ገድ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በኢየሩሳሌም የነበሩትም ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ገድለዋቸው ነበርና። የይሁዳም ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 22:1
12 交叉引用  

ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ሥጋ ዘመዶች ጥቂቶቹን አግኝቶ፣ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እኛ የአካዝያስ ሥጋ ዘመዶች ነን፤ ንጉሣዊውን ቤተ ሰብና የእቴጌዪቱን ልጆች ለመጠየቅ ወደዚህ ወርደን መጥተናል” አሉ።


የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት፣ የኢዮሣፍጥ ልጅ ይሆራም በይሁዳ ነገሠ።


ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ማኅበር አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ወገብህን ታጥቀህ፣ ይህን የዘይት ማሰሮ በመያዝ በራሞት ወደምትገኘው ገለዓድ ሂድ።


የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣


አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች፤ እርሷም የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።


ጉባኤው ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከንጉሡ ጋራ ቃል ኪዳን አደረጉ። ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለዳዊት ዘር በሰጠው ተስፋ መሠረት እነሆ፤ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል።


የእስራኤል ንጉሥ ዮአስም የአካዝያስን የልጅ ልጅ የኢዮአስን ልጅ የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስን ቤትሳሚስ ላይ ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ ከኤፍሬም በር እስከ ማእዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ ያህል ርዝመት ያለውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ።


ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ በሙሉ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት የነበረውን ዖዝያንን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ፈንታ አነገሡት።


ከዚያም የአገሩ ሕዝብ በንጉሥ አሞን ላይ ያሤሩትን ሁሉ ገደሉ፤ ልጁን ኢዮስያስንም በምትኩ አነገሡት።


የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወስደው በአባቱ ምትክ በኢየሩሳሌም አነገሡት።


跟着我们:

广告


广告