Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 21:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩ ዐረቦችን በኢዮራም ላይ በጠላትነት እንዲነሡ አደረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን የቊጣ መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በባሕር ዳርቻ ሰፍረው በነበሩት ኢትዮጵያውያን አጠገብ ፍልስጥኤማውያንና ዐረቦች ይኖሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም እነርሱን በኢዮራም ላይ ጦርነት እንዲያደርጉ አነሣሣቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን አጠ​ገብ የሚ​ኖ​ሩ​ትን የዓ​ረ​ብ​ያን ሰዎች በኢ​ዮ​ራም ላይ አስ​ነሣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔርም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 21:16
16 交叉引用  

እንደ ገናም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ዳዊትንም በእነርሱ ላይ በማስነሣት፣ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” አለው።


ስለዚህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “ይህን በማድረግህ ያዘዝሁህን ኪዳኔንና ሥርዐቴንም ባለመጠበቅህ፣ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጠዋለሁ፤


እግዚአብሔር ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ኤዶማዊውን ሃዳድን በሰሎሞን ላይ አስነሣው።


እግዚአብሔርም ከጌታው ከሱባ ንጉሥ አድርአዛር ኰብልሎ የነበረውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን ሌላ ጠላት አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣው፤


ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።


ከዐረቦች ጋራ ወደ ሰፈር የመጡት ወራሪዎች፣ ታላላቅ ወንድሞቹን ሁሉ ገድለዋቸው ስለ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይሆራምን የመጨረሻ ልጅ አካዝያስን በአባቱ ምትክ አነገሡት። ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ መግዛት ጀመረ።


እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን፣ በጉርበኣል በሚኖሩ ዐረቦችና በምዑናውያን ላይ ድልን አቀዳጀው።


ስለዚህ እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ እነርሱም በምናሴ አፍንጫ መንጠቆ አገቡበት፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያ ዓመት፣ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በግዛቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም እንዲጻፍ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤


ከዚያም እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም ቤተ ሰብ አለቆች እንዲሁም ካህናቱና ሌዋውያኑ ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመሥራት ተዘጋጁ።


ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤ የተመረጠውንም ንብረቴን ተሸክማችሁ ወደ ቤተ መቅደሳችሁ አስገብታችኋልና።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ ለኤዶም ሸጣለችና።


የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?


አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባሪያውን ቃል ያድምጥ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደ ሆነ፣ ቍርባን ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፤ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳድደውኛልና።


跟着我们:

广告


广告