Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 21:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከነቢዩ ከኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለኢዮራም መጣ፤ “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አንተ በአባትህ በኢዮሣፍጥ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ መጣለት፦ “የአባትህ የዳዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ነቢዩ ኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለኢዮራም ላከ፦ “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአባትህን የንጉሥ ኢዮሣፍጥን ወይም የአያትህን የንጉሥ አሳን መልካም ምሳሌነት አልተከተልክም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከነ​ቢ​ዩም ከኤ​ል​ያስ እን​ዲህ የሚል ጽሕ​ፈት መጣ​በት፥ “የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በአ​ባ​ትህ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ መን​ገድ፥ በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ መን​ገድ አል​ሄ​ድ​ህ​ምና፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ጽሕፈት መጣበት “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 21:12
14 交叉引用  

አሳ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ።


በዚህ ጊዜ ከገለዓድ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፣ “በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር፣ በሚቀጥሉት ዓመታት ዝናብ ወይም ጠል አይኖርም” አለው።


እርሱም በአካሄዱ ሁሉ የአባቱን የአሳን መንገድ ተከተለ፤ ከዚያም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔርም ፊት መልካም የሆነውን አደረገ፤ ይሁን እንጂ በየኰረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ገና አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በዚያ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር።


እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጌልገላ ተነሥተው ይጓዙ ነበር።


እያዘገሙም ሲነጋገሩ ሳለ፣ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ።


አብያ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አሳ በርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በዘመኑም በምድሪቱ ለዐሥር ዓመት ሰላም ሆነ።


“የብራና ጥቅልል ውሰድ፤ ለአንተም መናገር ከጀመርሁበት ከኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት አንሥቶ እስካሁን ድረስ ስለ እስራኤል፣ ስለ ይሁዳና ስለ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የነገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት፤


ይሁዲ ከብራናው ሦስት ወይም አራት ዐምድ ባነበበ ቍጥር ንጉሡ ብራናው ሁሉ እስከሚያልቅ ድረስ በጸሓፊ ቢላዋ እየቈረጠ እንዲቃጠል ወደ እሳቱ ምድጃ ይጥል ነበር።


በድንገትም የሰው እጅ ጣቶች ታዩ፤ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በመቅረዙ ትይዩ ባለው ግድግዳ ልስን ላይ ጻፉ፤ ንጉሡም ይጽፍ የነበረውን እጅ አየ፤


跟着我们:

广告


广告