Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 የመሪሳ ሰው የሆነው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር በኢዮሣፍጥ ላይ፣ “ከአካዝያስ ጋራ የስምምነት ውል ስለ አደረግህ፣ እግዚአብሔር ሥራህን ያፈርሰዋል” ሲል ትንቢት ተናገረበት፤ መርከቦቹም ተሰበሩ፤ ለንግዱም ሥራ መሄድ አልቻሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 የመሪሳም ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር፦ “ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና ጌታ ሥራህን አፍርሶታል” ብሎ በኢዮሣፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ። መርከቦቹም ተሰበሩ፥ ወደ ተርሴስም ለመሄድ አልቻሉም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ነገር ግን የማሬሻ ተወላጅ የሆነው የዶዳዋ ልጅ ኤሊዔዘር ኢዮሣፍጥን “ከአካዝያስ ጋር የስምምነት ውል ስላደረግህ እግዚአብሔር የሠራኸውን ሁሉ ያጠፋል” ሲል አስጠንቅቆት ስለ ነበር መርከቦቹ በሙሉ ተሰባበሩ፤ ከቶም በባሕር ላይ አልተጓዙም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 የማ​ር​ሶስ ሰው የኢ​ያ​ድያ ልጅ አል​ዓ​ዛር፥ “ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​ብ​ረ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን አፍ​ር​ሶ​ታል” ብሎ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገረ። መር​ከ​ቦ​ቹም ተሰ​በሩ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም ይሄዱ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 የመሪሳም ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር “ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና እግዚአብሔር ሥራህን አፍርሶታል” ብሎ በኢዮሣፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ። መርከቦቹም ተሰበሩ፤ ወደ ተርሴስም ይሄዱ ዘንድ አልቻሉም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:37
12 交叉引用  

ኢዮሣፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ይሁን እንጂ በዔጽዮንጋብር ስለ ተሰበሩ ከቶ ወደዚያ መሄድ አልቻሉም ነበር።


ጋት፣ መሪሳ፣ ዚፍ፣


በፍጹም ልባቸው የሚታመኑበትን ለማበርታት የእግዚአብሔር ዐይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመለከታሉና። የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራህ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”


ባለራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥንም እንዲህ አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ ባንተ ላይ ነው፤


ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦችን ለመሥራትም ተስማሙ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር አሠሩ።


ኢዮሣፍጥ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ ኢዮራምም በምትኩ ነገሠ።


ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር።


ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።


የአላዋቂነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።”


ምክንያቱም ጌታ የሚወድደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።”


እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።


跟着我们:

广告


广告