Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 2:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱም እናቱ ከዳን ወገን፣ አባቱም የጢሮስ አገር ሰው ነው፤ በወርቅና በብር፣ በናስና በብረት፣ በድንጋይና በዕንጨት፤ እንዲሁም በሐምራዊና በሰማያዊ፣ በቀይ ግምጃና በቀጭን በፍታ ሥራ የሠለጠነ ሲሆን፣ በልዩ ልዩ ቅርጻ ቅርጽ ሥራ ልምድ ያካበተና የተሰጠውን ማንኛውንም ንድፍ በሥራ መተርጐም የሚችል ባለሙያ ነው። እርሱም ከአንተ የእጅ ሥራ ባለሙያዎችና ከጌታዬ ከዳዊት የእጅ ሥራ ባለሙያዎች ጋራ ዐብሮ ይሠራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እናቱ ከዳን ልጆች ናት፥ አባቱም የጢሮስ ሰው ነው፤ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ድንጋይንና እንጨቱን፥ ሐምራዊውንና ሰማያዊውን ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ ለመሥራት፥ ቅርጽም ለመሥራት ንድፍም ለመንደፍ ሌላም ነገር ሁሉ ለማድረግ እውቀት አለው፥ እርሱም ከብልሃተኛዎችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር አብሮ ይሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የሑራም አቢ እናት ከዳን ነገድ ስትሆን፥ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ነው፤ ሑራም አቢ ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከድንጋይና ከእንጨት ልዩ ልዩ ነገሮችን የመሥራት ችሎታ አለው፤ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ጨርቅና ከበፍታ የተለያየ ልብስ መሥራት ይችላል፤ ከዚህም ሌላ ልዩ ልዩ ቅርጽ ማውጣትና በተሰጠውም ንድፍ መሠረት ሁሉን ነገር መሥራት ይችላል፤ ስለዚህ ይህን ሰው በእጅ ሥራ ከሠለጠኑ ከአንተ ሰዎችና ከእነዚያ ለአባትህ ይሠሩ ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲሠራ አድርገው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እናቱ ከዳን ልጆች ናት፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ነው፤ በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንና እን​ጨ​ቱን መለ​በጥ፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንና ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ መሥ​ራት፥ ቅር​ጽም፥ ሌላም ነገር ሁሉ ማድ​ረግ ያው​ቃል። ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችህ ጋር ከጌ​ታ​ዬም ከአ​ባ​ትህ ከዳ​ዊት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ሥራ ብለህ የም​ት​ሰ​ጠ​ውን ሁሉ አስቦ መሥ​ራት ይች​ላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እናቱ ከዳን ልጆች ናት፤ አባቱም የጢሮስ ሰው ነው፤ ወርቁንና ብሩንም፥ ናሱንና ብረቱን፥ ድንጋይንና እንጨቱን፥ ሐምራዊውንና ሰማያዊውን ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ ይሠራ ዘንድ፥ ቅርጽም ሌላም ነገር ሁሉ ያደርግ ዘንድ ያውቃል።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 2:14
4 交叉引用  

“እጅግ ብልኀተኛ የሆነውን ኪራም አቢን ልኬልሃለሁ፤


“ስለዚህ አንተ በወርቅና በብር፣ በናስና በብረት፣ በሐምራዊና በደማቅ ቀይ፣ በሰማያዊም ግምጃ ሥራ ዕውቀት ያለውን እንዲሁም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው ከእኔ የእጅ ባለሙያዎች ጋራ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የቅርጻ ቅርጽ ጥበብ ሥራ የሚሠራ ሰው ላክልኝ።


跟着我们:

广告


广告