Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ወደ ንጉሡ በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሚክያስ ሆይ፤ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ እንዝመት ወይስ እንቅር?” ሲል ጠየቀው። እርሱም መልሶ፣ “ሂዱና ድል አድርጉ፤ በእጃችሁ ዐልፈው ይሰጣሉና” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት እንሂድን? ወይስ ልቅር?” አለው። እርሱም መለልሶ እንዲህ አለው፦ “ውጣ፥ ይከናወንልህ፤ በእጅህም ተላልፈው ይሰጣሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ፥ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት? ወይስ እንተው?” ሲል ጠየቀው። ሚክያስም “ዝመትባት! በእርግጥም ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወደ ንጉ​ሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሚክ​ያስ ሆይ፥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንሂድን? ወይስ እንቅር?” አለው። እርሱም “ውጣ፤ ተከናወን፤ በእጅህም አልፈው ይሰጣሉ” አለ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:14
9 交叉引用  

እኩለ ቀንም ላይ ኤልያስ፣ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ፤ አምላክ አይደለም እንዴ! ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ወይም ሥራ በዝቶበት፣ አልያም በጕዞ ላይ ይሆናል፤ ተኝቶም ከሆነ ቀስቅሱት” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር።


ወደ ንጉሡ በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሚክያስ ሆይ፤ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ እንዝመት ወይስ እንቅር?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ሂዱና ድል አድርጉ እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” ብሎ መለሰለት።


ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማ እዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንም የአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ስድሳ ባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤


ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! አምላኬ የሚለውን ብቻ እነግረዋለሁ” አለ።


ንጉሡም፣ “ከእውነት በቀር ምንም ነገር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ የማምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው።


እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።


አንቺ በዖፅ ምድር የምትኖሪ፣ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ ነገር ግን ለአንቺም ደግሞ ጽዋው ይደርስሻል፤ ትሰክሪያለሽ፤ ዕርቃንሽንም ትጋለጫለሽ።


ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? እነሆ፤ ሰዓቱ ቀርቧል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ዐልፎ ይሰጣል፤


跟着我们:

广告


广告