Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 16:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ንጉሥ አሳም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነርሱም ባኦስ በራማ ሲሠራበት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት ወሰዱ፤ አሳም ጌባዕንና ምጽጳን ሠራበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ንጉሡም አሳ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነርሱም ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰዱ፥ እርሱም ጌባንና ምጽጳን ሠራበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ ንጉሥ አሳ ሰዎችን ከመላ ይሁዳ ሰብስቦ ንጉሥ ባዕሻ ራማን ለመመሸግ ይጠቀምበት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ከዚያ ወስደው የጌባዕንና የምጽጳን ከተማዎች መሸጉባቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የይ​ሁዳ ንጉሥ አሳም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ባኦስ ይሠ​ራ​በት የነ​በ​ረ​ውን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ እር​ሱም ገባ​ዖ​ን​ንና መሴ​ፋን ሠራ​በት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ንጉሡም አሳ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት አስወገዱ፤ እርሱም ጌባንና ምጽጳን ሠራበት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 16:6
14 交叉引用  

አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ዘመነ መንግሥታቸውን ያሳለፉት፣ እርስ በርስ በመዋጋት ነበር።


ንጉሥ አሳ አንድም ሰው እንዳይቀር በይሁዳ ሁሉ ዐዋጅ አስነገረ፤ ከዚያም ሕዝቡ ባኦስ በራማ ሲሠራበት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት አጋዘ፤ በእነርሱም ንጉሡ አሳ የብንያምን ጌባዕና ምጽጳን ሠራበት።


ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ ጌባዕን፣ ጋሌማን፣ ዓናቶትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉት እነዚህ ከተሞች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።


ባኦስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ራማን መገንባቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ።


በዚያ ጊዜም ባለራእዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ሳይሆን በሶርያ ንጉሥ ስለ ታመንህ፣ የሶርያ ንጉሥ ሰራዊት ከእጅህ አምልጧል።


እነርሱም በይሁዳ ላይ ወጡ፤ ወረሯትም። በንጉሡ ቤተ መንግሥት የሚገኘውን ዕቃ ሁሉ፣ ከወንዶች ልጆቹና ከሚስቶቹ ጋራ ወሰዱ፤ ከመጨረሻ ልጁ ከአካዝያስ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም።


መተላለፊያውን ዐልፈው እንዲህ ይላሉ፤ “በጊብዓ ሰፍረን እናድራለን።” ራማ ደነገጠች፤ የሳኦል ከተማ ጌባዕ ሸሸች።


ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ከርሱም ጋራ በምድሪቱ በቀረው ሕዝብ መካከል ኖረ።


ምድር ሁሉ ከጌባዕ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሪሞን ድረስ ተለውጣ ደልዳላ ሜዳ ትሆናለች፤ ኢየሩሳሌም ግን ከብንያም በር እስከ መጀመሪያው በር፣ ከማእዘን በርና ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ የወይን ጠጅ መጥመቂያ ድረስ በዚያው በቦታዋ ላይ ከፍ እንዳለች ትኖራለች።


ዲልዓን፣ ምጽጳ፣ ዮቅትኤል፣


ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ጠርቶ፣


በየዓመቱ በቤቴል፣ በጌልገላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፣ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።


እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ውሃ ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለት ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” ብለው ተናዘዙ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።


跟着我们:

广告


广告