Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 14:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አሳና ሰራዊቱም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዷቸው፤ እጅግ ብዙ ቍጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ስለ ወደቁም፣ ሊያንሰራሩ አልቻሉም፤ በእግዚአብሔር ፊትና በሰራዊቱ ፊት ተደመሰሱ። የይሁዳም ሰዎች እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፥ በጌታና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ የይሁዳ ሰዎችም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አሳና ሠራዊቱም እስከ ገራር ድረስ አሳደዱአቸው፤ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ብዙ ሰዎች ስላለቁ፥ ሠራዊቱ እንደገና ተንሠራርቶ ሊዋጋ አልቻለም፤ በዚህም ዐይነት ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ድል ሆኑ፤ የይሁዳ ሰዎችም እጅግ የበዛ ምርኮ ወሰዱ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አሳም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌዶር ሀገር ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንም ፈጽ​መው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ተሰ​ባ​ብ​ረ​ዋ​ልና፤ እጅ​ግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 14:13
17 交叉引用  

የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።


የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ስቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።


አብርሃም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ አካባቢ ሄዶ በቃዴስና በሱር መካከል ሰፈረ፤ ለጥቂት ጊዜም በጌራራ ተቀመጠ።


ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ፣ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። ይሥሐቅም የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ ወደሚኖርበት ወደ ጌራራ ሄደ።


ያንም ቦታ ለቅቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስለ ለቀቀባቸው የያዕቆብን ልጆች ያሳደዳቸው አልነበረም።


ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፣ ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጐርፉ ነበር።


ከግብጽ ዐብረውት የመጡትን ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሠረገላዎች፣ ስድሳ ሺሕ ፈረሰኞችና ስፍር ቍጥር የሌላቸውን የሊቢያ፣ የሱኪምና የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዞ፣


በጌራራ ዙሪያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ወደቀባቸው ከተሞቹን ሁሉ አጠፏቸው፤ እጅግ ብዙ ምርኮም በዚያ ስለ ነበር፣ በዘበዟቸው።


በዚያ ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለእግዚአብሔር ሠዉ።


በይሁዳ ዙሪያ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ስለ ወደቀባቸው ኢዮሣፍጥን አልተዋጉትም።


እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንዴት እንደ ተዋጋቸው በሰሙ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ወደቀባቸው።


እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣ ምነው እጁ በተፈታ!


ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤ እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጕዳት የሄደ ማን ነው?


እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም።


እነርሱም ከጌታ ፊትና ከኀይሉ ክብር ተወግደው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ፤


እርሱም፣ “አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ በመሆኔ እነሆ፤ መጥቻለሁ” ሲል መለሰለት፤ ኢያሱም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፣ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው።


“ጌታዬ የእግዚአብሔርን ጦርነት ስለሚዋጋ እግዚአብሔርም ለጌታዬ ሥርወ መንግሥቱን በርግጥ ለዘላለም የሚያጸናለት በመሆኑ፣ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ።


跟着我们:

广告


广告