Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 13:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ደግሞስ የአሮን ልጆች የሆኑትን የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያንን አባርራችሁ፣ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ፣ እናንተም የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁምን? አንድ ኰርማና ሰባት አውራ በግ ይዞ ራሱን ለመቀደስ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑ ለእነዚያ ጣዖታት ካህን ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የአሮንን ልጆች የጌታን ካህናትና ሌዋውያንን አላሳደዳችሁምን? እንደ ሌሎችም አሕዛብ ልማድ ለራሳችሁ ካህናትን አልሾማችሁምን? አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ ለመቀደስ የሚመጣ ሁሉ አማልክት ላልሆኑት ለእነዚያ ካህን ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የእግዚአብሔር ካህናት የሆኑትን የአሮንን ልጆች ሌዋውያንን አባረራችሁ፤ በእነርሱም ምትክ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ ለራሳችሁ ካህናትን ሾማችኋል፤ አንድ ወይፈንና ሰባት በጎች ይዞ ራሱን ለመለየት ወደ እናንተ የሚመጣውን ማንኛውንም ሰው ሐሰተኞች ለሆኑት አማልክታችሁ ካህን አድርጋችሁ ትሾማላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የአ​ሮ​ንን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን አላ​ሳ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ለራ​ሳ​ችሁ ካህ​ና​ትን አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምን? አንድ ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዞ ራሱን ይቀ​ድስ ዘንድ የሚ​መጣ ሁሉ አማ​ል​ክት ላል​ሆ​ኑት ለእ​ነ​ዚያ ካህን ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የአሮንን ልጆች፥ የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያን አላሳደዳችሁምን? እንደ ሌሎችም አሕዛብ ልማድ ካህናትን አላደረጋችሁምን? አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ ይቀድስ ዘንድ የሚመጣ ሁሉ አማልክት ላልሆኑት ለእነዚያ ካህን ይሆናል።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 13:9
19 交叉引用  

ይህም ሁሉ ሆኖ ኢዮርብዓም ከክፉ መንገዱ አልተመለሰም፤ ይልቁንም በኰረብታ ማምለኪያዎች ከሁሉም የሕዝብ ክፍል እንደ ገና ካህናትን ይሾም ጀመር፤ ካህን ለመሆን የሚፈልገውንም ሁሉ ለየኰረብታ ማምለኪያዎቹ ለየ።


አማልክታቸውን በእሳት ውስጥ ጥለው አቃጥለዋቸዋል፤ በሰው እጅ የተሠሩ ዕንጨትና ድንጋይ ብቻ እንጂ አማልክት አልነበሩምና።


እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በየእጅ ጥበብ ባለሙያ ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው?”


“ለእኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱንም አልተውንም፤ እግዚአብሔርን በማገልገል ላይ ያሉት ካህናት የአሮን ልጆች ሲሆኑ፣ ረዳቶቻቸውም ሌዋውያኑ ናቸው።


ከዚያም ሕዝቅያስ፣ “እነሆ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል፤ አሁንም ቅረቡ፤ መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ” አላቸው። ስለዚህ ጉባኤው መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ አመጡ፤ ልባቸው የፈቀደ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።


“ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርገው ይህ ነው፤ ነቀፋ የሌለባቸው አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ውሰድ።


“የአሮን የተቀደሱ ልብሶች ለትውልዶቹ ይሆናሉ፤ ይኸውም በእነርሱ ይቀቡና ክህነትን ይቀበሉ ዘንድ ነው።


“ክህነታቸውን በሰባት ቀን በመፈጸም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ያዘዝሁህን ሁሉ አድርግላቸው።


ከዚያም ሙሴ፣ “በራሳችሁ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ላይ በመነሣታችሁ፣ በዛሬዋ ቀን ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ሆናችኋል፤ በዛሬዋም ዕለት ባርኳችኋል” አለ።


የእውነት አማልክት ባይሆኑም እንኳ፣ አማልክቱን የለወጠ ሕዝብ አለን? ሕዝቤ ግን ክብራቸው የሆነውን፣ በከንቱ ነገር ለወጡ።


“ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤ እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።


ይህም በእስራኤል ሆነ! የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክ አይደለም፤ ያ የሰማርያ ጥጃ፣ ተሰባብሮ ይደቅቃል።


ሊቀ ካህናት ለመሆን አባቱን በመተካት የተቀባና የተሾመ ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤


“አሮንንና ልጆቹን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ የመቅቢያ ዘይቱን፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን መሶብ አምጣ፤


ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የእስያ አውራጃ የሚገኘውን በርካታ ሕዝብ እያሳመነ እንዳሳታቸው ይኸው የምታዩትና የምትሰሙት ነገር ነው፤ በሰው እጅ የተሠሩ አማልክት በፍጹም አማልክት እንዳልሆኑ ይናገራልና።


እግዚአብሔርን ከማወቃችሁ በፊት፣ በባሕርያቸው አማልክት ላልሆኑት ባሪያዎች ነበራችሁ፤


አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፦ ላላወቋቸው አማልክት፣ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፣ አባቶቻችሁ ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ።


跟着我们:

广告


广告