Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 30:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋራ የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋራ አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋር የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋር አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እናንተ በምትሉት ነገር ማንም አይስማማበትም! ወደ ኋላ ቀርቶ ጓዝ ሲጠብቅ የቈየውም ሆነ ወደ ጦርነት የዘመተው ሁሉም የተገኘውን ምርኮ እኩል መካፈል አለበት” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ይህ​ንስ ነገር ማን ይሰ​ማ​ች​ኋል? እና​ንተ ከእ​ነ​ርሱ አት​በ​ል​ጡ​ምና ወደ ጦር​ነት በሄ​ዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠ​በቁ ሰዎች ድርሻ እን​ዲሁ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ይህንስ ነገር ምን ይሰማችኋል? ነገር ግን የተዋጉትና ዕቃውን የጠበቁት እድል ፈንታ እኩል ይሆናል፥ አንድነት ይካፈላሉ አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 30:24
7 交叉引用  

“የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤ በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።


ምርኮውንም ለሁለት ከፍላችሁ በጦርነቱ ለተካፈሉት ወታደሮችና ለቀረው ማኅበረ ሰብ አከፋፍሉት።


እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ ሀብት ይዛችሁ ማለትም አያሌ የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ናስና ብረት እንዲሁም ቍጥሩ እጅግ የበዛ ልብስ ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ ከጠላት የተገኘውንም ይህን ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋራ ተካፈሉት” አላቸው።


የተጨነቁ፣ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ አራት መቶ ያህል ሰዎች፣ ወደ እርሱ ተሰባሰቡ፤ መሪያቸውም ሆነ።


ዳዊትም ሰዎቹን፣ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋራ ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።


ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር ይህን ማድረግ አይገባችሁም።


ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ለእስራኤል ደንብና ሥርዐት አደረገው።


跟着我们:

广告


广告