Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 29:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አሁንም ዐብረውህ ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋራ ማለዳ ተነሡ፤ በጧት ፀሓይ እንደ ወጣችም ሂዱ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሁንም አብረውህ ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማለዳ ተነሡ፤ በጥዋት ፀሐይ እንደ ወጣችም ሂዱ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህ አንተና ከአንተ ጋር የመጡ የጌታህ አገልጋዮች ነገ ጠዋት ሲነጋጋ በመነሣት ወደ ሰፈራችሁ ተመለሱ” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም አንተ ከአ​ን​ተም ጋር የመጡ የጌ​ታህ ብላ​ቴ​ኖች ማል​ዳ​ችሁ ተነሡ፤ ሲነ​ጋም ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ወደ መጣ​ች​ሁ​በት ሂዱ። ክፉ ነገ​ር​ንም በል​ብህ አታ​ኑር፤ በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ ነህና፥ በነ​ጋም ጊዜ ገሥ​ግ​ሣ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ሂዱ” አለው። እነ​ር​ሱም ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም አንተ ከአንተም ጋር የመጡ የጌታህ ባሪያዎች ማልዳችሁ ተነሡ፥ ሲነጋም ተነሥታችሁ ሂዱ አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 29:10
8 交叉引用  

ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።


ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ተባብሮ ሳኦልን ለመውጋት በሄደ ጊዜ፣ ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ከድተው ከዳዊት ሰራዊት ጋራ ተቀላቀሉ። እርሱ ግን ርዳታ አላደረገላቸውም፤ ምክንያቱም የፍልስጥኤማውያን ገዦች ምክር ካደረጉ በኋላ እንዲህ ሲሉ ልከውት ነበር፤ “ከድቶ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ቢሄድ እኛን ያስጨርሰናል።”


ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፣ ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጐርፉ ነበር።


በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።


ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።


ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ለመመለስ በማለዳ ተነሡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።


跟着我们:

广告


广告