1 ሳሙኤል 26:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ሳኦልም፣ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ስለ ከበረች፣ ከእንግዲህ ወዲያ አልጐዳህም፤ በርግጥ የሞኝ ሥራ ሠርቻለሁ፤ እጅግ ሲበዛም ተሳስቻለሁ” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ሳኦልም፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ስለከበረች ከእንግዲህ ወዲያ አልጐዳህም፤ ይሄው፥ የሞኝ ሥራ ሠራሁ፤ አብዝቼም ተሳሳትኩ” አለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፤ እነሆ፥ ስንፍና እንደ አደረግሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወቅሁ” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ሳኦልም፦ በድያለሁ፥ ልጄ ሆይ ዳዊት፥ ተመለስ፥ ዛሬ ነፍሴ በዓይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፥ እነሆ፥ ስንፍና አድርጌአለሁ፥ እጅግ ብዙም ስቻለሁ አለ። 参见章节 |