Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 19:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱም ልብሱን አውልቆ፣ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ዕራቍቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፣ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠረ?” ያለው በዚህ ምክንያት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም ልብሱን አውልቆ፥ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ራቁቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፥ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቆጠረ?” ካለው የተነሣ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወደ ሳሙኤልም ፊት ሲቀርብ ልብሱን አውልቆ ትንቢት እየተናገረ፤ ቀኑንም ሌሊቱንም ሁሉ ራቁቱን በዚያው ተጋድሞ ዋለ፤ “ሳኦልም ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠርን?” የሚለው የምሳሌ አነጋገር የመነጨው ከዚህ የተነሣ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ልብ​ሱ​ንም አወ​ለቀ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ፤ ራቁ​ቱ​ንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ ተጋ​ደመ። ስለ​ዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት መካ​ከል ነውን?” ይባ​ባሉ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ልብሱንም አወለቀ፥ በሳሙኤልም ፊት ትንቢት ተናገረ፥ ራቁቱንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚያም ሌሊት ሁሉ ተጋደመ። ስለዚህ፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት መካከል ነውን? ይባባሉ ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 19:24
10 交叉引用  

ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኀይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይጨፍር ነበር።


ዳዊት ቤተ ሰቡን ለመመረቅ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ፣ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጥታ፣ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ አንድ ተራ ሰው ዕራቍቱን መታየቱ ክብሩ ሆኖ ነው!” አለችው።


በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።


በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤ እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ።


የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣ ሁሉን ቻይ የአምላክን ራእይ የሚያይ፣ ከመሬት የተደፋው ዐይኖቹም የተከፈቱለት ሰው ንግር፤


የሰሙትም ሁሉ በመገረም፣ ይህ ሰው “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረ አይደለምን? ደግሞም ወደዚህ የመጣው እነርሱን አስሮ ወደ ካህናት አለቆች ሊወስዳቸው አልነበረምን?” አሉ።


የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ይወርድብሃል፤ ከእነርሱ ጋራ ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።


ሳሙኤል ለሳኦል ቢያለቅስለትም እንኳ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ዳግመኛ ሊያየው አልሄደም፤ እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጸተ።


በማግስቱም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በኀይል መጣበት፣ በዚህ ጊዜ ዳዊት ወትሮ እንደሚያደርገው ሁሉ በገና ሲደረድር፣ ሳኦል በቤቱ ሆኖ ትንቢት ይናገር ነበር። ሳኦል በእጁ ጦር ይዞ ነበር፤


跟着我们:

广告


广告