Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም፣ “ሂድ፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋራ ይሁን” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ ጌታ አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሲል ዳዊት ተናገረ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ ጌታ ካንተ ጋር ይሁን!” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ከአንበሳና ድብ ያዳነኝ እግዚአብሔር ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም “መልካም ነው! እንግዲህ ሂድ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን!” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ዳዊትም፦ ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:37
21 交叉引用  

እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሠኘውን ያድርግ።”


“አሁንም ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሁን፤ እንድትፈጽመው በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ያብቃህ።


እነዚህም ቍጥራቸው እጅግ የበዛ የወርቅ፣ የብር፣ የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው። በል ሥራህን ጀምር፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋራ ይሁን።”


በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ” ለምን ትሏታላችሁ?


እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?


በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤ ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።


አንተ ረዳቴ ነህና፣ በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።


የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤ የጥንት ታምራትህን በርግጥ አስታውሳለሁ፤


ንጉሥ ሆይ፤ በሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ብንጣል፣ የምናመልከው አምላክ ሊያድነን ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል።


ለሙሴ ሙሉ በሙሉ እንደ ታዘዝን ሁሉ፣ ለአንተም እንታዘዛለን፤ ብቻ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበረ፣ አሁንም ከአንተ ጋራ ይሁን።


በዚሁ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፤ ዐጫጆቹንም፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን!” ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው። እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ!” ብለው መለሱለት።


ባሪያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።


ከዚያም ሳኦል ለዳዊት የገዛ ራሱን የጦር ልብስ አለበሰው፤ ጥሩር አጠለቀለት፤ ከናስ የተሠራ ቍርም ደፋለት።


ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፣ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፣ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። እግዚአብሔር ከአባቴ ጋራ እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋራ ይሁን።


ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጕዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ማን ነው? ዛሬ ስላደረግህልኝ ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ።


ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ታላቅ ነገር ታደርጋለህ፤ በርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።


ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ ስሙንም “እግዚአብሔር እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው።


跟着我们:

广告


广告