1 ሳሙኤል 17:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ከእነርሱም ጋራ በሚነጋገርበት ጊዜ፣ ከጋት የመጣው ፍልስጥኤማዊው ጀግና ጎልያድ ከሰልፉ መካከል ወጥቶ እንደ ለመደው ሲደነፋ፤ ዳዊት ሰማ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ከእነርሱም ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ፥ እነሆ፥ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊው ጀግና ጎልያድ ከሰልፉ መካከል ወጥቶ እንደ ለመደው ሲደነፋ ዳዊት ሰማ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ዳዊትም ከወንድሞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ግዙፍ ፍልስጥኤማዊ የጋት ሰው ከዚያ በፊት ያደርገው እንደ ነበር ወደፊት በማምራት በእስራኤላውያን ላይ መፎከሩን ቀጠለ፤ ዳዊትም የእርሱን ድንፋታ ሰማ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለ ያ አርበኛ ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፤ ቀድሞ የተናገረውንም ቃል ተናገረ፤ ዳዊትም ሰማ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ያ ዋነኛ ጀግና ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፥ የተናገረውንም ቃል ተናገረ፥ ዳዊትም ሰማ። 参见章节 |