1 ሳሙኤል 16:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከአገልጋዮቹም አንዱ፣ “መልካም አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፣ እርሱም ጀግናና ተዋጊ ነው፤ በአነጋገሩ አስተዋይና የደስ ደስ ያለው ነው፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ነው” ብሎ መለሰ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “መልካም አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን የቤተልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እርሱም ጀግናና ተዋጊ ነው፤ በአነጋገሩ አስተዋይና የደስ ደስ ያለው ነው፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነው” ብሎ መለሰ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከአገልጋዮቹም አንዱ “የቤተልሔም ከተማ ነዋሪ የሆነው እሴይ በገና መደርደር የሚችል ልጅ እንዳለው አይቼአለሁ ይህም ብቻ ሳይሆን ጀግና፥ መልከ ቀና፥ ብርቱ ወታደርና ንግግር ዐዋቂ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፤ ሰውየውም ጠቢብ፥ ተዋጊም ነው፤ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፦ እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና የሚመታ የቤተ ልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እርሱም ጽኑዕ ኃይል ነው፥ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው አለ። 参见章节 |