Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 14:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ስለዚህ ሳኦል እንዲህ አለ፤ “የሰራዊቱ መሪዎች ሁላችሁም ወደዚህ ቅረቡ፤ ዛሬ ምን ኀጢአት እንደ ተሠራ እንወቅ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ሳኦል እንዲህ አለ፦ “እናንተ የሕዝቡ አለቆች ሁሉ፥ ወደዚህ ቅረቡ፥ ዛሬ ይህ ኃጢአት በምን እንደሆነ እወቁ፥ ተመልከቱም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ከዚህ በኋላ ሳኦል ለሕዝቡ መሪዎች እንዲህ አለ፤ “ወደዚህ ቀርባችሁ ዛሬ ምን ዐይነት ኃጢአት እንደ ተሠራ መርምራችሁ ዕወቁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ሳኦ​ልም፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ችን ሁሉ ወደ​ዚህ አቅ​ርቡ፤ ዛሬ ይህ ኀጢ​ኣት በማን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38-39 ሳኦልም፦ እናንተ የሕዝቡ አለቆች ሁሉ፥ ወደዚህ ቅረቡ፥ ዛሬ ይህ ኃጢአት በምን እንደ ሆነ እወቁ፥ ተመልከቱም፥ እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኃጢአቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 14:38
11 交叉引用  

ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ከቁም ነገር አይቈጥሩንም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት ደንታቸው አይደለም፣ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺሕ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።


ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋራ፣ የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤ የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና፤ እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።


ከይሁዳ፣ የማእዘን ድንጋይ፣ የድንኳን ካስማ፣ የጦርነት ቀስት፣ ገዥም ሁሉ ይወጣል።


“አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል። የሞዓብን ግንባሮች፣ የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቅቃል።


ኢየሱስም፣ “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማእዘን ራስ ሆነ፤ ጌታ ይህን አድርጓል፤ ይህም ለዐይናችን ድንቅ ነው።’ ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን አላነበባችሁምን?” አላቸው።


በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤


እስራኤል በድሏል፤ እንዲጠብቁ ያዘዝኋቸውን ቃል ኪዳኔን ጥሰዋል፤ ዕርም የሆነውን ነገር ወስደዋል፤ ሰርቀዋል፤ ዋሽተዋል፤ የወሰዱትንም ከራሳቸው ንብረት ጋራ ደባልቀዋል።


እንግዲህ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ለመቋቋም ያልቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። ጀርባቸውን አዙረው የሸሹትም ለጥፋት በመዳረጋቸው ነው። ዕርም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ፣ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋራ አልሆንም።


የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ሁሉ ቍጥራቸው አራት መቶ ሺሕ በሚሆን፣ ሰይፍ በሚመዝዙ እግረኞች ወታደሮች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ መካከል ተገኙ።


跟着我们:

广告


广告