Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፣ “ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፣ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ በደስታ ፈነደቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከያቤሽ የመጡትንም መልእክተኞች “ነገ ከቀትር በፊት የምናድናቸው መሆኑን ለሕዝባችሁ ንገሩ” አሉአቸው። መልእክቱንም ለያቤሽ ሰዎች በነገሩ ጊዜ የያቤሽ ሰዎች እጅግ ተደሰቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የመ​ጡ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተ​ኰሰ ጊዜ ድኅ​ነት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል በሉ​አ​ቸው” አሉ​አ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የመጡትንም መልክተኞች፦ የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኮሰ ጊዜ ማዳን ይሆንላችኋል በሉአቸው አሉአቸው። መልክተኞችም መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፥ ደስም አላቸው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 11:9
7 交叉引用  

እርሱም የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ይህን እንዲነግሩ መልእክተኞች ላከ፤ “በእንዲህ ዐይነት ሁኔታ ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር በጎነት አሳይታችኋልና እግዚአብሔር ይባርካችሁ፤


ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።


ከዚያም፣ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከኢያቢስ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤


ለኢያቢስም ሰዎች፣ “እኛ ነገ እጃችንን እንሰጣችኋለን፤ እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ” አሏቸው።


ሳኦል ቤዜቅ በተባለ ስፍራ ሰራዊቱን በሰበሰበ ጊዜ፤ ቍጥራቸው ከእስራኤል ሦስት መቶ ሺሕ፣ ከይሁዳም ሠላሳ ሺሕ ነበር።


የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፣


跟着我们:

广告


广告