Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 10:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጐሣው ወደ ፊት አቀረበ፤ የማጥሪ ጐሣም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ። እርሱ ግን ተፈልጎ አልተገኘም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየወገኑ ወደ ፊት አቀረበ፤ የማጥሪ ቤተሰብም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ። እርሱ ግን ተፈልጎ አልተገኘም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እንደገናም ሳሙኤል፥ የብንያም ነገድ ቤተሰቦች ሁሉ ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከነዚያም የማጥሪ ቤተሰብ በዕጣ ተመረጠ፤ በመጨረሻም የማጥሪ ቤተሰብ ወንዶች ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከእነርሱም መካከል ለቂስ ልጅ ለሳኦል ዕጣ ወጣ፤ እነርሱም በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የብ​ን​ያ​ም​ንም ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በማ​ጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማ​ጥ​ር​ንም ወገን በየ​ሰዉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በቂስ ልጅ በሳ​ኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለ​ገ​ውም፤ አላ​ገ​ኘ​ው​ምም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፥ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 10:21
7 交叉引用  

እንዲሁም አበኔር ለብንያማውያን ራሱ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ።


ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።


ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።


ከዚያም ሕዝቡ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለመኑት፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን፣ የቂስን ልጅ ሳኦልን ሰጣቸው፤ እርሱም አርባ ዓመት ገዛቸው።


ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ ባቀረበ ጊዜ፣ የብንያም ነገድ ተመረጠ።


ሰዎቹም፣ “ሰውየው መጥቷልን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ነገር ግን በዕቃ መካከል ተሸሽጓል” አለ።


ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።


跟着我们:

广告


广告