Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 1:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ይህን ያህል ጊዜ የጸለይሁት ከባድ ከሆነው ጭንቀቴና ሐዘኔ የተነሣ ስለ ሆነ፣ አገልጋይህን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቍጠረኝ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ይህን ያህል ጊዜ የጸለይኩት ከባድ ከሆነው ጭንቀቴና መከራዬ የተነሣ ስለሆነ፥ አገልጋይህን እንደማትረባ ሴት አትቁጠረኝ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔን አገልጋይህን እንደማትረባ ሴት አድርገህ አትቊጠረኝ፤ ይህን ያኽል በማስረዘም የጸለይኩት መከራ የበዛብኝ ችግረኛ በመሆኔ ነው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ኀዘ​ኔና ጭን​ቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁና ባር​ያ​ህን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሴቶች ልጆች አት​ቍ​ጠ​ራት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ ተናግሬአለሁና ባሪያህን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቍጠረኝ ብላ መለሰችለት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 1:16
11 交叉引用  

ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስልኝም። በውስጤ ታውኬአለሁ፤ ተናውጬአለሁም፤


ምናምንቴ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፣ “ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ” በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፣


ጕዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፣


ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ሰክሬ አይደለም፤ እኔ ልቧ ክፉኛ የታወከባት ሴት ነኝ፤ ልቤን በእግዚአብሔር ፊት አፈሰስሁ እንጂ፣ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም።


ዔሊም፣ “በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ” ሲል መለሰላት።


አንዳንድ ምናምንቴ ሰዎች ግን፣ “እንዲህ ያለ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” በማለት ናቁት፤ ስጦታም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።


የዔሊ ልጆች ምናምንቴ ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር።


ጌታዬ፣ ያን ምናምንቴ ሰው ናባልን ከቁም ነገር አይቍጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለ ሆነ፣ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም ዐብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጕልማሶች አላየኋቸውም።


跟着我们:

广告


广告