Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 4:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማ እዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንም የአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ስድሳ ባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በሬማት ዘገለዓድ የጌበር ልጅ ነበረ፤ ለእርሱም በገለዓድ ያሉት የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች ነበሩ፤ ለእርሱም ደግሞ በባሳን በአርጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥርና የናስ መወርወሪያዎች የነበረባቸው ስድሳ ታላላቅ ከተሞች ነበሩበት፤

参见章节 复制




1 ነገሥት 4:13
14 交叉引用  

የእስራኤልም ንጉሥ ሹማምቱን፣ “በገለዓድ የምትገኘው ራሞት የእኛ ሆና ሳለች፣ ከሶርያው ንጉሥ እጅ ለመመለስ ምንም እንዳላደረግን አታውቁምን?” አላቸው።


ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ማኅበር አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ወገብህን ታጥቀህ፣ ይህን የዘይት ማሰሮ በመያዝ በራሞት ወደምትገኘው ገለዓድ ሂድ።


ስለዚህ የናሜሲ የልጅ ልጅ፣ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ አሤረ። በዚህ ጊዜ ኢዮራምና እስራኤል ሁሉ በራሞት የምትገኘውን ገለዓድን ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጥቃት ለማዳን ይጠብቁ ነበር።


ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።


ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።


አንተ ብርቱ ተራራ፣ የባሳን ተራራ ሆይ፤ አንተ ባለብዙ ጫፍ ተራራ፣ የባሳን ተራራ፤


ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር መኖሪያቸውን ወስዶ፣ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው።


በከፍታው ቦታ ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ገለዓድን እንዳለ፣ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ያለውን ባሳንን ሁሉ እንዲሁም በባሳን ውስጥ የሚገኙትን የዐግ ግዛት ከተሞች በእጃችን አደረግን።


በዚያ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ የዐግ ግዛት ከሆነው፣ በባሳን ከሚገኘው ከጠቅላላው የአርጎብ ክልል ስድሳ ከተሞች ውስጥ፣ እኛ ያልያዝነው አንድም ከተማ አልነበረም።


ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኘውን፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ ያለውን ግዛት፣ ከእነዚህ ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ላይ ወሰድንባቸው።


ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።


እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ።


ከጋድ ነገድ፣ በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣


跟着我们:

广告


广告