Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 3:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች። ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጇ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርሷ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርሷም አይሁን! ለሁለት ይቆረጥ!” አለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርስዋ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርስዋም አይሁን! ለሁለት ይቈረጥ!” አለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ደኅ​ነ​ኛ​ውም ሕፃን የነ​በ​ራት ሴት አን​ጀ​ትዋ ስለ ልጅዋ ታው​ኳ​ልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይ​ደ​ለም፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ለእ​ር​ስዋ ስጣት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት” ብላ ለን​ጉሡ ተና​ገ​ረች። ያች​ኛ​ዪቱ ግን፥ “አካ​ፍ​ሉን እንጂ ለእ​ኔም ለእ​ር​ስ​ዋም አይ​ሁን” አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ደኅነኛውም የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ናፍቆአልና “ጌታዬ ሆይ! ደኀነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ አትግደል፤” ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛይቱ ግን “ይከፈል እንጂ ለእኔም ለአንቺም አይሁን፤” አለች።

参见章节 复制




1 ነገሥት 3:26
12 交叉引用  

ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለ ተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰወር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ።


በዚህ ጊዜ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ልጅ ከሁለት ክፈሉና ለአንዷ ግማሹን፣ ለሌላዪቱም ግማሹን ስጡ” ብሎ አዘዘ።


ከዚህ በኋላ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለመጀመሪያዪቱ ሴት ስጧት፤ አትግደሉት፤ እናቱ እርሷ ናት” አለ።


ልቤ በውስጤ ጋለ፤ በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤


“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!


ኤፍሬም የምወድደው፣ ደስም የምሰኝበት ልጄ አይደለምን? ብዙ ጊዜ ተቃውሜው ብናገርም፣ መልሼ ስለ እርሱ ዐስባለሁ፤ አንጀቴ ይላወሳል፤ በታላቅ ርኅራኄም እራራለታለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።


“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።


የማያስተውሉ፣ ውል የሚያፈርሱ፣ ርኅራኄ የሌላቸውና ጨካኞች ናቸው።


በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያህል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።


ከክርስቶስ ጋራ ካላችሁ አንድነት የተነሣ የትኛውም መበረታታት፣ ከፍቅር የሆነ መጽናናት፣ የመንፈስ ኅብረት፣ ምሕረትና ርኅራኄ ካላችሁ፣


ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣


ማንም የዚህ ዓለም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ልቡ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በርሱ ይኖራል?


跟着我们:

广告


广告