1 ነገሥት 3:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ንጉሡም፣ “ይህችኛዪቱ፣ ‘የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው፣ የአንቺ የሞተው ነው’ ትላለች፤ ያችኛዪቱ ደግሞ፣ ‘አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቷል፣ በሕይወት ያለው የእኔ ነው’ ትላለች” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን “አንደኛዋ ‘በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!’ ትላለች፤ ሌላይቱ ደግሞ ‘አይደለም! የአንቺ ልጅ ሞቷል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው!’ ትላታለች አለ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን “አንደኛዋ ‘በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!’ ትላለች፤ ሌላይቱ ደግሞ ‘አይደለም! የአንቺ ልጅ ሞቶአል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው!’ ትላታለች አለ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በዚያ ጊዜም ንጉሡ፥ “አንቺ፦ ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው ትያለሽ፤ አንቺም፦ አይደለም የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው ትያለሽ”። አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 በዚያን ጊዜም ንጉሡ “ይህች ‘ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው፤’ ትላለች፤ ያችኛይቱም ‘አይደለም፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው፤’ ትላለች፤” አለ። 参见章节 |