Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 22:48 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ኢዮሣፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ይሁን እንጂ በዔጽዮንጋብር ስለ ተሰበሩ ከቶ ወደዚያ መሄድ አልቻሉም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 በዚያን ዘመን የኤዶም ምድር የራስዋ ንጉሥ አልነበራትም፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ንጉሥ በሚሾመው እንደ ራሴ ትገዛ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዐይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 ኢዮሣፍጥም ወደ ኦፊር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ የተርሴስን መርከቦች ሠራ፤ ነገር ግን መርከቦቹ በዔጽዮንጋብር ተሰበሩ እንጂ አልሄዱም።

参见章节 复制




1 ነገሥት 22:48
18 交叉引用  

ይሥሐቅም ለዔሳው፣ “በአንተ ላይ የበላይነት እንዲኖረው፣ ወንድሞቹ ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ፣ እህሉ፣ የወይን ጠጁም የተትረፈረፈ እንዲሆንለት መርቄዋለሁ። ታዲያ ልጄ፣ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” ሲል መለሰለት።


በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር።


በዚያ ጊዜም የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ኢዮሣፍጥን “ሰዎቼ ከሰዎችህ ጋራ በመርከብ ይሂዱ” ሲል ጠይቆት ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ዕሺ አላለውም።


እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ጠረፍ፣ በኤላት አጠገብ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።


እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን አመጡ።


ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ከይሁዳ ንጉሥና ከኤዶም ንጉሥ ጋራ ለመዝመት ተነሣ። ሰባት ቀን ከዞሩም በኋላ ለሰራዊቱም ሆነ ለእንስሶቻቸው የተረፈ ውሃ አልነበረም።


በይሆራም ዘመነ መንግሥት፣ ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐምፆ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።


ከሕዝቡም ጋራ ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ።


ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እርሱ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤልም ሆነ ከማናቸውም የኤፍሬም ሕዝብ ጋራ አይደለምና፣ እነዚህ የእስራኤል ወታደሮች ከአንተ ጋራ አይዝመቱ።


ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር።


ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።


የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣ አንተ አብረከረክሃቸው።


የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣ የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።


በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣ የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።


ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፤ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጕዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።


跟着我们:

广告


广告