1 ነገሥት 21:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከዚያም ለኤልዛቤል፣ “ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ ሞቷል” ብለው ላኩባት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 አክዓብም፦ “በማን?” አለ፥ እርሱም፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በአውራጆቹ አለቆች ጉልማሶች’” አሉ፤ እርሱም፦ “ሰልፉን ማን ይጀምራል?” አለ፤ እርሱም፦ “አንተ” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 “ናቡቴ ተወግሮ ተገድሎአል” የሚል መልእክትም ወደ ኤልዛቤል ላኩ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አክዓብም፥ “በምን አውቃለሁ?” አለ፤ እርሱም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጃዎቹ አለቆች ጐልማሶች” አለ፤ አክዓብም፥ “ውጊያውን ማን ይጀምራል?” አለ፤ እርሱም፥ “አንተ” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አክዓብም፦ በማን? አለ፤ እርሱም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጆቹ አለቆች ጕልማሶች አለ፤ እርሱም፦ ሰልፉን ማን ይጀምራል? አለ፤ እርሱም፦ አንተ አለው። 参见章节 |