Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 20:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ስለዚህ ለቤን ሃዳድ መልእክተኞች፣ “ለጌታዬ ለንጉሡ፣ ‘እኔ ባሪያህ በመጀመሪያ ያልኸኝን ሁሉ አደርጋለሁ፤ ያሁኑን ጥያቄህን ግን ልፈጽመው አልችልም’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። መልእክተኞቹም ይህንኑ ይዘው ተመለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ስለዚህም አክዓብ ለቤንሀዳድ መልእክተኞች “ለጌታዬ ለንጉሡ፥ ከዚህ በፊት ባቀረብክልኝ ጥያቄ ተስማምቼ ነበር፤ አሁን ባቀረብክልኝ በሁለተኛው ጥያቄ ግን ልስማማበት አልችልም ብሏል ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። መልእክተኞቹም ተመልሰው በመሄድ መልሱን ነገሩት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህም አክዓብ ለቤንሀዳድ መልእክተኞች “ለጌታዬ ለንጉሡ፥ ‘ከዚህ በፊት ባቀረብክልኝ ጥያቄ ተስማምቼ ነበር፤ አሁን ባቀረብክልኝ በሁለተኛው ጥያቄ ግን ልስማማበት አልችልም ብሎአል’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። መልእክተኞቹም ተመልሰው በመሄድ መልሱን ነገሩት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የዚ​ያች ደብ​ዳ​ቤም ቃል እን​ዲህ ይላል፥ “ጾምን ጹሙ፤ ናቡ​ቴ​ንም በሕ​ዝቡ መካ​ከል በከ​ፍ​ተኛ ቦታ አስ​ቀ​ም​ጡት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በደብዳቤውም “ስለ ጾም አዋጅ ንገሩ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀምጡት፤

参见章节 复制




1 ነገሥት 20:9
3 交叉引用  

አሳም ከእግዚአብሔር ቤትና ከራሱም ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የቀረውን ብርና ወርቅ በሙሉ ወሰደ፤ ከዚያም በሹማምቱ እጅ በደማስቆ ተቀምጦ ይገዛ ለነበረው፣ ለጠብሪሞን ልጅ፣ የአዚን የልጅ ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ለቤን ሃዳድ ላከ።


ከዚያም ቤን ሃዳድ፣ “ለሚከተለኝ ሰው ሁሉ የሰማርያ ዐፈር አንዳንድ ዕፍኝ የሚዳረስ ሳይሆን ቢቀር፣ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ሲል ሌሎች መልክተኞችን ወደ አክዓብ ላከ።


ሽማግሌዎቹና ሕዝቡም ሁሉ፣ “የሚልህን አትቀበለው፤ የጠየቀህንም ዕሺ አትበለው” አሉት።


跟着我们:

广告


广告