Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 20:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ አክዓብ የየአውራጃው አዛዥ የሆኑትን ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ወጣት መኰንኖች ጠራ፤ ከዚያም የቀሩትን እስራኤላውያን ሰበሰበ፤ እነዚህም በአጠቃላይ ሰባት ሺሕ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ ንጉሡ ብዛታቸው ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ብቻ የሆነ በአውራጃ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ሥር የሆኑትን ወጣትነት ያላቸውን ወታደሮች ጠራ፤ ቀጥሎም ጠቅላላ ብዛቱ ሰባት ሺህ የሆነ የእስራኤልን ሠራዊት ጠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ንጉሡ ብዛታቸው ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ብቻ የሆነ በአውራጃ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ሥር የሆኑትን ወጣትነት ያላቸውን ወታደሮች ጠራ፤ ቀጥሎም ጠቅላላ ብዛቱ ሰባት ሺህ የሆነ የእስራኤልን ሠራዊት ጠራ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ኤል​ዛ​ቤ​ልም በሰ​ማች ጊዜ አክ​ዓ​ብን፥ “ናቡቴ ሞቶ​አል እንጂ በሕ​ይ​ወት አይ​ደ​ለ​ምና በገ​ን​ዘብ ይሰ​ጥህ ዘንድ እንቢ ያለ​ውን የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ ተነ​ሥ​ተህ ውረስ” አለ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኤልዛቤልም ናቡቴ ተወግሮ እንደ ሞተ በሰማች ጊዜ ኤልዛቤል አክዓብን “ናቡቴ ሞቶአል፤ በሕይወትም አይደለምና በገንዘብ ይሰጥህ ዘንድ እንቢ ያለውን የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ቦታ ተነሥተህ ውረስ፤” አለችው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 20:15
11 交叉引用  

እኔም ጕልበታቸው ለበኣል ያልተንበረከከውንና አፋቸው ምስሉን ያልሳመውን ሰባት ሺሕ ሰዎች በእስራኤል አስቀራለሁ።”


አክዓብም፣ “ይህን የሚያደርገው ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን የሚያደርጉት የየአውራጃው አዛዥ የሆኑ ወጣት መኰንኖች ናቸው’ ” አለው። “ታዲያ ጦርነቱን የሚጀምረው ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም፣ “አንተው ትጀምራለህ” ብሎ መለሰ።


እነርሱም ቤን ሃዳድና ከርሱ ጋራ ተባብረው የነበሩት ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሰክረው ሳለ እኩለ ቀን ላይ መጡ።


ከኢዮአካዝ ሰራዊት የተረፈው ዐምሳ ፈረሰኞች፣ ዐሥር ሠረገሎችና ዐሥር ሺሕ እግረኛ ወታደር ብቻ ነው፤ ይህ የሆነበትም ምክንያት የሶርያ ንጉሥ የቀረውን ስለ አጠፋውና እንደ ዐውድማ ብናኝ ስለ አደረገው ነበር።


በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ደካሞችን ከኀይለኞች የሚታደግ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ታምነናልና፣ ይህን ታላቅ ሰራዊት በስምህ እንገጥመዋለን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም።”


ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።


ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፣ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።


እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፣ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደ የመጡበት ይመለሱ” አለው።


ሳኦልም በጊብዓ ዳርቻ ሚግሮን በተባለ ስፍራ ከአንድ የሮማን ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር፤ ስድስት መቶ ያህል ሰዎችም ዐብረውት ነበሩ፤


ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና፤ ወደነዚያ ሸለፈታሞች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን እግዚአብሔርን የሚያግደው የለምና” አለው።


跟着我们:

广告


广告