Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 18:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 በሰባተኛው ጊዜ አገልጋዩ፣ “እነሆ፤ የሰው እጅ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕሩ እየወጣች ነው” አለው። ኤልያስም፣ “ሂድና አክዓብን፣ ‘ዝናቡ ሳያግድህ፣ ሠረገላህን ጭነህ ውረድ’ ብለህ ንገረው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የም​ታ​ህል ትንሽ ደመና ከባ​ሕር ውኃ ቋጥራ ስት​ወጣ አየሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ወጥ​ተህ አክ​ዓ​ብን፦ ዝናብ እን​ዳ​ይ​ዝህ ሰረ​ገ​ላ​ህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 በሰባተኛውም ጊዜ “እነሆ፥ የሰው እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባሕር ወጣች፤” አለ። እርሱም “ወጥተህ አክዓብን ‘ዝናብ እንዳይከለክልህ ሠረገላን ጭነህ ውረድ፤’ በለው፤” አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 18:44
7 交叉引用  

አገልጋዩንም፣ “ውጣና ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ተመለከተና፤ “በዚያ ምንም የለም” አለው። ኤልያስ ሰባት ጊዜ፣ “እንደ ገና ሂድ” አለው።


ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።


እናንተ በለኪሶ የምትኖሩ፣ ፈረሶችን ከሠረገላው ጋራ አያይዙ፤ ለጽዮን ሴት ልጅ፣ የኀጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፤ የእስራኤል በደል በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና።


“የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱ በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”


ደግሞም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ደመና በምዕራብ በኩል ሲወጣ ስታዩ ወዲያው፣ ‘ዝናብ ሊመጣ ነው’ ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል፤


እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው።


“ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው።


跟着我们:

广告


广告