Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 16:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱም የሰማርያን ኰረብታ በሁለት መክሊት ጥሬ ብር ከሳምር ላይ ገዝቶ ከተማ ሠራባት፤ ስሟንም በቀድሞው የተራራዋ ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከዚያም በኋላ ሼሜር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያን ኰረብታ በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛ፤ ዖምሪ ኰረብታውን ከመሸገ በኋላ ከተማ ቆረቆረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሼሜር ስም “ሰማርያ” ብሎ ሰየማት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚያም በኋላ ሼሜር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያን ኰረብታ በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛ፤ ዖምሪ ኰረብታውን ከመሸገ በኋላ ከተማ ቈረቈረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሼሜር ስም “ሰማርያ” ብሎ ሰየማት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ዘን​በ​ሪም ከዚ​ያች ተራራ ባለ​ቤት ከሴ​ሜር በሁ​ለት መክ​ሊት ብር የሳ​ም​ሮ​ንን ተራራ ገዛ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠ​ራ​ት​ንም ከተማ በተ​ራ​ራው ባለ​ቤት በሳ​ምር ስም ሰማ​ርያ ብሎ ጠራት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ከሳምርም በሁለት መክሊት ብር የሰማርያን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ሠራ፤ የሠራውንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 16:24
16 交叉引用  

በቤቴል ባለው መሠዊያ፣ በሰማርያ ከተሞችና በየኰረብታው ባሉ ማምለኪያ ስፍራዎች ላይ በእግዚአብሔር ቃል ጮኾ ያሰማው መልእክት በትክክል የሚፈጸም ነውና።”


ሰማርያ ላይ በሠራውም የበኣል ቤተ ጣዖት ለበኣል መሠዊያ አቆመለት።


ስለዚህም ኤልያስ ራሱን በአክዓብ ፊት ለመግለጥ ሄደ። በዚህ ጊዜ ራብ በሰማርያ ክፉኛ ጸንቶ ነበር።


በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ቤን ሃዳድ መላ ሰራዊቱን በአንድነት አሰባሰበ፤ ከርሱም ጋራ ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው ዐብረውት ነበሩ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከብቦ ወጋት።


ንጉሡ ስለ ሞተም ወደ ሰማርያ አምጥተውት እዚያው ተቀበረ።


በዚህ ጊዜ አክዓብ በሰማርያ ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስለዚህ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ ለኢይዝራኤል ሹማምት፣ ለሽማግሌዎችና የአክዓብን ልጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ወደ ሰማርያ ላከ፤ መልእክቱም እንዲህ የሚል ነበር፤


የይሁዳ ንጉሥ ዖዝያን በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የኢያቤስ ልጅ ሰሎም በእስራኤል ላይ ነገሠ። በሰማርያ ተቀምጦ አንድ ወር ገዛ።


የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፣ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዘጠኝ ዓመትም ገዛ።


የአሦርም ንጉሥ ሕዝቡን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋና ከሐማት፣ ከሴፈርዋይም ከተሞች አምጥቶ በእስራኤላውያን ቦታ እንዲገቡ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነርሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ ይኖሩ ጀመር።


በሆሴዕ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም በምርኮ ወደ አሦር አፈለሳቸው። እነዚህም በአላሔ፣ ጎዛን ውስጥ በአቦር ወንዝ አጠገብ እንዲሁም በማዴ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


ሰማንያ ሰዎች ጢማቸውን ተላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀድደው፣ ገላቸውን ነጭተው የእህል ቍርባንና ዕጣን በመያዝ ከሴኬም፣ ከሴሎና ከሰማርያ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማቅረብ መጡ።


በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣ በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣ እናንተ የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!


ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለ ያዕቆብ በደል፣ ስለ እስራኤልም ቤት ኀጢአት ነው። የያዕቆብ በደል ምንድን ነው? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ የኰረብታ መስገጃ ምንድን ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?


跟着我们:

广告


广告