Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 16:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚህ ሁኔታም በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የባኦስን ቤተ ሰብ ሁሉ ፈጀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚህም ዓይነት ጌታ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በነ​ቢዩ በኢዩ አፍ በባ​ኦስ ቤት ላይ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 ባኦስና ልጁ ኤላ ስለ ሠሩት ኀጢአት ሁሉ፥ በምናምንቴም ሥራቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቆጡት ዘንድ እስራኤልን ስለ አሳቱበት ኀጢአት፥ በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዘምሪ የባኦስን ቤት ሁሉ እንዲሁ አጠፋ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 16:12
11 交叉引用  

ከዚያም ቀበሩት፤ እግዚአብሔር በባሪያው በአኪያ አማካይነት እንደ ተናገረ፣ እስራኤል ሁሉ አለቀሱለት።


አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ዘመነ መንግሥታቸውን ያሳለፉት፣ እርስ በርስ በመዋጋት ነበር።


ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ሲል ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ፤


ስለዚህ ባኦስንና ቤቱን ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ ቤትህንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት አደርገዋለሁ።


ከዚህም በቀር የእግዚአብሔር ቃል በአናኒ ልጅ፣ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤቱ ላይ የመጣበት ምክንያት፣ በእጁ ሥራ ያስቈጣው ዘንድ እንደ ኢዮርብዓም ቤት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሁሉ በማድረጉና ኢዮርብዓምን በማጥፋቱም ጭምር ነው።


በኤልያስ በተነገረው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም ነበርና።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በጋትሔፌር ነቢይ፣ በአማቴ ልጅ በባሪያው በዮናስ አማካይነት እንደ ተናገረው፣ ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ እስከ ሙት ባሕር ድረስ የነበረውን የእስራኤልን ድንበር አስመለሰ።


እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአኪያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ስለ ወሰነ፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።


ባለራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥንም እንዲህ አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ ባንተ ላይ ነው፤


የቀረውም ኢዮሣፍጥ በዘመነ መንግሥቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ያከናወናቸው ተግባራት፦ የአናኒ ልጅ ኢዩ በዘገበው የእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቧል።


በሞኝ እጅ መልእክትን መላክ፣ የገዛ እግርን እንደ መቍረጥ ወይም መርዝ እንደ መጋት ነው።


跟着我们:

广告


广告