Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 15:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ወዲያውኑ እንደ ነገሠም የኢዮርብዓምን ቤተ ሰብ በሙሉ ፈጀ። እግዚአብሔር በሴሎናዊው ባሪያው በአኪያ በኩል እንደ ተናገረው፣ ከኢዮርብዓም ቤተ ሰብ አንድም ሰው በሕይወት ሳያስቀር፣ ሁሉንም አጠፋቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ወዲያውኑም የኢዮርብዓምን ቤተሰብ አባላት ሁሉ መፍጀት ጀመረ፤ ጌታ የሴሎ ተወላጅ በሆነው በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት የኢዮርብዓም ቤተሰብ በሙሉ ተገደሉ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ወዲያውኑም የኢዮርብዓምን ቤተሰብ አባላት ሁሉ መፍጀት ጀመረ፤ እግዚአብሔር የሴሎ ተወላጅ በሆነው በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት የኢዮርብዓም ቤተሰብ በሙሉ ተገደሉ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከነ​ገ​ሠም በኋላ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ወገን ሁሉ አጠፋ፥ በባ​ሪ​ያው በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ እጅ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋው ድረስ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ወገን ሕይ​ወት ያለ​ውን አላ​ስ​ቀ​ረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29-30 ንጉሥም በሆነ ጊዜ የኢዮርብዓምን ቤት ሁሉ መታ፤ ኢዮርብዓምም ስለ ሠራው ኀጢአት፥ እስራኤልንም ስላሳተበት፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ስላስቆጣበት ማስቆጫ፥ በባሪያው በሴሎናዊው በአኪያ እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል እስኪያጠፋው ድረስ ከኢዮርብዓም አንድ ትንፋሽ ያለው አላስቀረም።

参见章节 复制




1 ነገሥት 15:29
12 交叉引用  

ይህም ኀጢአት የኢዮርብዓም ቤት እንዲወድቅና ከምድር ገጽም እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ።


ባኦስ ናዳብን የገደለውና በእግሩ ተተክቶ የነገሠው፣ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው።


ዘምሪ ወዲያው እንደ ነገሠና በዙፋን እንደ ተቀመጠ፣ የባኦስን ቤተ ሰብ በሙሉ ገደለ፤ የሥጋ ዘመድም ሆነ ወዳጅ አንድም ወንድ አላስቀረም።


ስለዚህ ባኦስንና ቤቱን ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ ቤትህንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት አደርገዋለሁ።


ከዚህም በቀር የእግዚአብሔር ቃል በአናኒ ልጅ፣ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤቱ ላይ የመጣበት ምክንያት፣ በእጁ ሥራ ያስቈጣው ዘንድ እንደ ኢዮርብዓም ቤት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሁሉ በማድረጉና ኢዮርብዓምን በማጥፋቱም ጭምር ነው።


ለቍጣ ስላነሣሣኸኝና እስራኤልንም ስላሳትሃቸው፣ ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት፣ እንደ አኪያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደርገዋለሁ።’


ነገር ግን ኢዩ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ሕግ በፍጹም ልቡ ለመጠበቅ ጥንቃቄ አላደረገም፤ ኢዮርብዓም፣ እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልራቀምና።


“ ‘ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት፣ አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣ አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።


跟着我们:

广告


广告