Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 15:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ናዳብና መላው እስራኤል በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከብበው ሳሉ፣ ከይሳኮር ነገድ የተወለደው የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐምፆ በመነሣት ናዳብን በገባቶን ገደለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባዕሻ በናዳብ ላይ ዐምፆ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባዕሻ በናዳብ ላይ ዐምፆ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከበ​ለ​ዓን ቤት የሆነ የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ ዐመ​ፀ​በት፤ ናባ​ጥና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ገባ​ቶ​ንን ከብ​በው ነበ​ርና ባኦስ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ልም ሀገር ባለው በገ​ባ​ቶን ገደ​ለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ከይሳኮርም ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ተማማለበት፤ ናዳብና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤም አገር ባለው በገባቶን ገደለው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 15:27
15 交叉引用  

“ከዚህም በላይ፣ እግዚአብሔር የኢዮርብዓምን ቤተ ሰብ የሚያስወግድ ንጉሥ በእስራኤል ላይ ለራሱ ያስነሣል፤ ይህም ዛሬ፣ አሁኑኑ ይሆናል።


ባኦስ ናዳብን የገደለውና በእግሩ ተተክቶ የነገሠው፣ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው።


ዘምሪም ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ እግር ተተክቶ፣ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ነገሠ።


የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሆኖ ሰባት ቀን ብቻ ገዛ። በዚህ ጊዜ ሰራዊቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ የሆነችውን ገባቶንን ከብቦ ሰፍሮ ነበር።


በዚያም ሰፈር የነበሩ እስራኤላውያን ዘምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን እንደ ሰሙ፣ የሰራዊቱን አዛዥ ዖምሪን በዚያ ዕለት እዚያው ሰፈር ውስጥ በእስራኤል ላይ ማንገሣቸውን ዐወጁ።


ከዚያም ዖምሪና ዐብረውት ያሉት እስራኤላውያን ሁሉ ከገባቶን ወደ ላይ ወጥተው ቴርሳን ከበቡ።


ከዚህም በቀር የእግዚአብሔር ቃል በአናኒ ልጅ፣ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤቱ ላይ የመጣበት ምክንያት፣ በእጁ ሥራ ያስቈጣው ዘንድ እንደ ኢዮርብዓም ቤት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሁሉ በማድረጉና ኢዮርብዓምን በማጥፋቱም ጭምር ነው።


ከሹማምቱ አንዱና የግማሽ ሠረገሎቹ አዛዥ የሆነው ዘምሪ ዐምፆ ተነሣበት፤ በዚያ ጊዜ ኤላ በቴርሳ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፤


ሹማምቱም በርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት።


ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።


ስለዚህ የናሜሲ የልጅ ልጅ፣ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ አሤረ። በዚህ ጊዜ ኢዮራምና እስራኤል ሁሉ በራሞት የምትገኘውን ገለዓድን ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጥቃት ለማዳን ይጠብቁ ነበር።


ሶርያውያንም በወጡ ጊዜ ኢዮአስን ክፉኛ አቍስለው፣ ጥለውት ሄዱ፤ የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ስለ ገደለም፣ ሹማምቱ አሢረውበት በዐልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በዳዊት ከተማ ተቀበረ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልተቀበረም።


ኤልተቄ፣ ገባቶን፣ ባዕላት፣


እንዲሁም ከዳን ነገድ፣ ኤልተቄን፣ ገባቶን፤


跟着我们:

广告


广告