1 ነገሥት 14:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 አሁንም ሂጂና ኢዮርብዓምን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ብለሽ ንገሪው፤ ‘ከሕዝቡ መካከል አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‘ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‘ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሂጂ ለኢዮርብዓም እንዲህ በዪው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከሕዝብ መካከል ለይቼ ከፍ አድርጌህ ነበር፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይም ንጉሥ አድርጌህ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ሂጂ፤ ለኢዮርብዓምም እንዲህ በዪው ‘የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከሕዝብ መካከል ለይቼ ከፍ አድርጌህ ነበር፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ አድርጌህ ነበር፤ 参见章节 |