Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 11:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 አንተን ግን እኔ እወስድሃለሁ፤ ልብህ በወደደው ሁሉ ላይ ትነግሣለህ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ትሆናለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አደርግሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አደርግሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 አን​ተ​ንም እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ነፍ​ስ​ህም በወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ላይ አነ​ግ​ሥ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 አንተንም እወስድሃለሁ፤ ነፍስህም በወደደችው ሁሉ ላይ ትነግሣለች፤ በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ትሆናለህ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 11:37
7 交叉引用  

ከዚያም አበኔር ዳዊትን፤ “ከአንተ ጋራ ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፣ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ሄጄ፣ ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።


እንዲሁም ከሰሎሞን ሹማምት አንዱ የሆነው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በንጉሡ ላይ ዐመፀ፤ እርሱም ከጸሬዳ የመጣ ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ እናቱ ጽሩዓ የተባለች መበለት ነበረች።


ስሜ እንዲኖርባት በመረጥኋት በዚያች በኢየሩሳሌም ከተማ ለባሪያዬ ለዳዊት ምን ጊዜም በፊቴ መብራት እንዲኖረው፣ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጣለሁ።


ባሪያዬ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ አንተም ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ በመንገዴ ብትሄድ፣ ሥርዐቴንና ትእዛዜን በመጠበቅ ትክክል የሆነውን ነገር በፊቴ ብታደርግ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ የዳዊትን ሥርወ መንግሥት እንዳጸናሁ፣ ለአንተም አጸናልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጣለሁ።


ኢዮርብዓም መመለሱን እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ጉባኤያቸው በማስጠራት በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት። ለዳዊት ቤት በታማኝነት ጸንቶ የተገኘው የይሁዳ ቤት ብቻ ነው።


አሁንም ሂጂና ኢዮርብዓምን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ብለሽ ንገሪው፤ ‘ከሕዝቡ መካከል አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤


በብሩም ደስ ያለህን ሁሉ፣ ማለትም የቀንድ ከብት፣ በግ፣ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ ብርቱ መጠጥ ወይም የምትሻውን ሁሉ ግዛበት። ከዚያም አንተና ቤተ ሰብህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በዚያ ትበላላችሁ፤ ሐሤትም ታደርጋላችሁ።


跟着我们:

广告


广告